መመሪያ
በዚህ ርዕስ ውስጥ የጆሮ ጤና ልየታ እንዴት ማከናወን እንደሚችሉ ይማራሉ።
አዘጋጅ
- ከእያንዳንዱ የጆሮ ጤና ምርመራ በፊት እና በኋላ (በሳሙና ወይም በሳኒታይዘር ጄል) ሁል ጊዜ እጅዎን ይታጠቡ እና ያድርቁ
- ልጁን በመብራት (ኦቶስኮፕ) የጆሮዎቻቸው ውስጠኛ ክፍል እንደሚመለከቱት ያስታውሱት።

ለጆሮ ጤና ልየታ ኦቶስኮፕ እና ስፔኩለም ይጠቀሙ።
- የኦቶስኮፕ መብራት እየሰራ መሆኑን ያረጋግጡ
- በልጁ ጆሮ ውስጥ በምቾት ሊገጥም የሚችለውን የስፔኩለም መጠን ይምረጡ
- ከእያንዳንዱ የጆሮ ጤና ምርመራ በፊት እና በኋላ ስፔኩሉን በጥጥ እና በፀረ-ተዋሲያን ያፅዱ
- ስፔኩለምን በኦቶስኮፕ ላይ ያስቀምጡት።
ጥያቄ
የጆሮውን ውስጠኛውን ክፍል ለመመልከት ምን አይነት ስፔኩለም መጠቀም አለብዎት?
አንዱን ይምረጡ።
መ ከመረጡ ትክክል ነዎት!
የተለያዩ ሰዎች የተለያየ የጆሮ ቱቦ መጠን አላቸው። ወደ ጆሮ ቱቦ ውስጥ በምቾት የሚገጥመውን ሁል ጊዜ ይምረጡ።
የጆሮ ጤና ልየታ

ከጆሮው ውጭ
መመሪያ
ኦቶስኮፕ በመጠቀም የጆሮው ውጫዊ ክፍል ጤናማ መሆኑን ያረጋግጡ።

- ይቀመጡ ወይም ጎንበስ ይበሉ እና የእያንዳንዱን ጆሮ ውጫዊ ክፍል በግልፅ ማየት እንዲችሉ የኦቶስኮፕ ብርሃን ይጠቀሙ
- የጆሮ ጤና ችግር ምልክቶችን ለማግኘት ከኋላ እና ከፊት ይመልከቱ
- ውጤቱን በልየታ ቅጽ ላይ ይመዝግቡ።
ውጤቶች፡-
- ሁለቱም ጆሮዎች ጤናማ የሚመስሉ ከሆነ አዎ ይምረጡ
- አንድ ወይም ሁለቱም ጆሮዎች ጤናማ ካልሆኑ አይ የሚለውን ይምረጡ እና ምክንያቱን ይመዝግቡ።
የማለፊያ ውጤትን ለመመዝገብ ሁለቱም ጆሮዎች ጤናማ መሆን አለባቸው። አንድ ወይም ሁለቱም ጆሮዎች ጤናማ ካልሆኑ ሪፈር ያድርጉ።
ጠቃሚ ምክር
ልጁ ጭንቅላቱውን ሳያንቀሳቅስ መቆየት ከተቸገረ፤ ሌላ አዋቂ ሰው በጆሮ ጤና ልየታ ወቅት ጭንቅላቱን በእርጋታ ይይዛል።
ትራገስን ይጫኑ
መመሪያ
ልጁ ህመም የሚሰማው መሆኑን ለማረጋገጥ ትራገሱን በቀስታ ይጫኑ ።

በሁለቱም ጆሮዎች ላይ ትራገስን ሲጫኑ ልጁ ህመም ከተሰማው፤ ይህ የጆሮ ኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል።
ውጤቱን በልየታ ቅጽ ላይ ይመዝግቡ።
ውጤቶች፡-
- አይ ለሁለቱም ጆሮዎች አልፏል
- ለየትኛውም አዎ ከሆነ የጆሮ ጤና ልየታውን ያቁሙ እና ሪፈር ያድርጉ።
በጆሮው ውስጥ
መመሪያ
ኦቶስኮፕ በመጠቀም የልጁ የጆሮ ቱቦ እና ታምቡር ጤናማ መሆናቸውን ያረጋግጡ።
ጆሮውን ያዘጋጁ
ኦቶስኮፕን የማይዝ እጅን በመጠቀም የጆሮውን ጀርባ በቀስታ ወደ ኋላ ይጎትቱ። ይህም የልጁ የጆሮ ቱቦ ውስጥ ለማየት ቀላል ያደርገዋል።

ኦቶስኮፕ መያዝ
የልጁን የቀኝ ጆሮ እየመረመሩ ከሆነ ኦቶስኮፕን በቀኝ እጅዎ ይያዙ እና የልጁን የግራ ጆሮ እየመረመሩ ከሆነ በግራ እጅዎ ይያዙ።
እስክሪብቶ እንደሚይዙ ኦቶኮስኮፕን ይያዙ።
ጠቃሚ ምክር
ኦቶስኮፕ ለማረጋጋት ትንሽ ጣትዎን በልጁ ጉንጭ ላይ ያሳርፉ።

ስፔኩለሙን አስገባ
ስፔኩለሙን ወደ ጆሮው ቱቦ ውስጥ በጥልቀት አያስገቡ። በሐሳብ ደረጃ የስፔኩለሙን ርዝመት ከግማሽ በላይ ማስገባት አያስፈልግም።
ስፔኩለሙን በትክክለኛ አቅጣጫ እንዲገባ ባለማድረግ ወይም በጥልቀት ወደ ውስጥ በማስገባት ህመም ሊከሰት ይችላል። ህመም በውጫዊ ጆሮ ኢንፌክሽን ምክንያት ሊከሰት ይችላል።
ማስጠንቀቂያ
ህመምን ወይም ጉዳትን ላለማድረስ ሁል ጊዜ ኦቶስኮፕን ቀስ ብለው ያስገቡ። ልጁ ህመም ከተሰማው የጆሮውን የጤና ምርመራ ያቁሙ።
ወደ ጆሮ እንክብካቤ ባለሙያዎችን ሪፈር ያድርጉ።
የጆሮ ቱቦ
ኦቶስኮፕ በመጠቀም የልጁን የጆሮ ቱቦ ውስጠኛ ክፍል ይመልከቱ።
ሁለቱም ጆሮዎች ጤናማ ከመሰሉ አዎ የሚለው ላይ የራይት ምልክት ያድርጉ።
አንድ ወይም ሁለቱም ጆሮዎች ጤናማ ካልሆኑ እና ከሚከተሉት ውስጥ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ምልክቶች ካላቸው አይ የሚለው ላይ የራይት ምልክት ያድርጉ፦
- ህመም
- እብጠት
- መቅላት
- መመንጨት
- የተደፈነ ጆሮ (የጆሮ ሰም ወይም ባዕድ አካል)።
ውጤቶች፡-
- ለሁለቱም ጆሮዎች አዎ ከሆነ በመዝገብ ቅጹ ላይ ይህንን ይመዝግቡ፤ አልፏል
- አይ ከሆነ ለአንድ ወይም ለሁለቱም ጆሮዎች ሪፈር ያድርጉ እና ምክንያቱ ላይ የራይት ምልክት ያድርጉበት።
ተግባር
ከታች ያሉትን ምስሎች ይመልከቱ። የጆሮ ቱቦ ጤናማ ይመስላልን?

አይ ልክ ነው!
የጆሮው ቱቦ ቀይ እና ያበጠ ነው።

አዎ ልክ ነው!
የእብጠት፣ የመቅላት፣ የፈሳሽ ምልክት የለም። ጆሮው አልተደፈነም (ሰም ወይም ባዕድ አካል)።
የጆሮ ታምቡር
ሁለቱም የጆሮ ታምቡር ጤናማ መሆናቸውን ለማየት በኦቶስኮፕ ይመልከቱ።
የጆሮ ታምቡር ማየት ካልቻሉ በሚከተሉት ምክንያቶች ሊሆን ይችላል፦
- መደፈን ወይም
- ኦቶስኮፕ በትክክል አልተቀመጠም።
ይህ የሚረዳ ከሆነ፤ የኦቶስኮፑን ቦታ በቀስታ ያስተካክሉ።
- ሁለቱም የጆሮ ታምቡር ጤናማ የሚመስሉ ከሆነ አዎ ብለው የራይት ምልክት ያድርጉ
- አንድ ወይም ሁለቱም የጆሮ ታምቡር ጤናማ ካልሆኑ የራይት ምልክት ያድርጉ No እና ምክንያቱን ይመዝግቡ፡-
- የጆሮ ታምቡር ማየት አልተቻለም
- በጆሮ ታምቡር ላይ እብጠት እና / ወይም መቅላት
- ቀዳዳዎች (ሽንቁር)።
ውጤቶች፡-
- ለሁለቱም ጆሮዎች አዎ ከሆነ በመዝገብ ቅጹ ላይ አልፏል
- አይ ከሆነ ለአንድ ወይም ለሁለቱም ጆሮዎች ሪፈር ያድርጉ እና የዚህ ምክንያቶች ላይ የራይት ምልክት ያድርጉ።
ተግባር
ከታች ያለውን ምስል ይመልከቱ፡-

የጆሮ ታምቡር ማየት ይችላሉ?
አይ ልክ ነው!
የጆሮው ቱቦ አብጧል እና ታምቡሩ እንዳይታይ አድርጓል። የጆሮ ታምቡር ማየት አይችሉም።
ዶ ዩን አስታውስ?

በዶ ዮን የጆሮ ጤና ልየታወቅት ልየታ አድራጊው ሰም በግራ ጆሮው ላይ ያለውን የጆሮ ቱቦ እንደደፈነ አረጋግጧል።
የልየታ አድራጊው ሰሙ እንዲወገድ ወደ አካባቢው የጆሮ እንክብካቤ ባለሙያዎች መራው።
ዶ ዮን ከአንድ ወር በኋላ እንደገና ተመርምሮ ለሁለቱም ጆሮዎች ማለፊያ ውጤት አግኝቷል።
መመሪያ
የጆሮ ጤና ልየታ ቪዲዮውን ይመልከቱ።
ጥያቄ
የጆሮ ጤና ልየታ ደረጃዎችን ከ 1 እስከ 4 በመቁጠር በትክክለኛው ቅደም ተከተል ያደራጁ።
ትክክለኛዎቹ እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦
- ኦቶኮስኮፕ ያዘጋጁ እና ተስማሚውን የስፔኩለም መጠን ይምረጡ
- ኦቶስኮፕን በመጠቀም የጆሮውን ውጫዊ ክፍል ይፈትሹ
- የጆሮን ውስጠኛ ክፍል ለመመልከት ጆሮውን በትክክል ይያዙት
- የጆሮ ቱቦ እና ታምቡር ይፈትሹ
በሁለቱም በኩል መድገም እንዳለብዎት ያስታውሱ!
ተግባር
የጆሮ ጤና ልየታ ማከናወንን ይለማመዱ።
መመሪያ
ማንኛውንም የመስማት ወይም የጆሮ ጤና ልየታ ከልጁ ጋር ማጠናቀቅ የማይቻል ከሆነ፤ ሪፈር የመደረግን አስፈላጊነት ከወላጆች ጋር ይወያዩ።