መመሪያ
በዚህ ርዕስ ውስጥ ስለ እይት እና የመስማት እንክብካቤ ይማራሉ።
የማየት እና የመስማት ችግር
አንዳንድ ልጆች ማየትም ወይም መስማት እንደ ሌሎች ሰዎች አይችሉም። አንዳንዶቹ ማየትም ሆነ መስማት አይችሉም።
ልጆች የማየት ወይም የመስማት ወይም የሁለቱም ችግሮች ሊያጋጥማቸው ይችላል።
ችግሮች በብዙ ምክንያቶች ሊከሰቱ ይችላሉ። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
- በሽታዎች ወይም የጤና ሁኔታዎች
- በአይን ወይም በጆሮ ውስጥ ኢንፌክሽኖች
- በአይን ወይም በጆሮ ላይ የሚደርስ ጉዳት።
መከላከል እና እንክብካቤ
አብዛኛዎቹ የአይን እና የጆሮ ጤና ችግሮች በእነዚህ መንገዶች ሊወገዱ ወይም ሊረዱ ይችላሉ-
- የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች
- ሕክምና
- አጋዥ ምርቶች
- ማገገሚያ(Rehabilitation)።
መመሪያ
አብዛኛው የአይን ወይም የጆሮ ጤና ችግር እንዴት መከላከል ወይም መቆጣጠር እንደሚቻል ለበለጠ መረጃ የዓለም ጤና ድርጅት የጤና ማስተዋወቂያ ቁሳቁሶችን ለትምህርት እድሜአቸው ለደረሱ ልጆች የእይታ እና የመስማት ማጣሪያ ምርመራ የትግበራ መመሪያ መጽሃፍ ይመልከቱ።
ጥያቄ
ዋናዎቹ የመከላከያ እና እንክብካቤ ቦታዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
ሀ. የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች
ለ. ሕክምና
ሐ. አጋዥ ምርቶች
መ. ማገገሚያ
በሳጥኑ ውስጥ ሀ፣ ለ፣ ሐ ወይም መ ፊደል በመጻፍ የሚከተሉትን ተግባራት ከትክክለኛው የመከላከያ እና እንክብካቤ ጋር ያዛምዱ።
ሀ. ጤናማ ዓይኖችን ለመጠበቅ ከቤት ውጭ መጫወት
ሐ. መነጽር ወይም የመስሚያ አጋዦች
መ. የምልክት ቋንቋ ወይም ብሬይል እንዴት መጠቀም እንደሚቻል መማር
ለ. ለኢንፌክሽን መድሃኒቶች ወይም ለአይን እና ጆሮ ጉዳት የአደጋ ጊዜ እንክብካቤ
ውይይት
ለሚከተሉት ፍላጎቶች በአጠገብዎ ምን አይነት አገልግሎቶች አሉ፦
- የአደጋ ጊዜ የዓይን ወይም የጆሮ እንክብካቤ
- የዓይን ወይም የጆሮ ኢንፌክሽን ሕክምና
- የመነጽር ወይም የመስሚያ አጋዦች አቅርቦት።
የሚከተሉት ከተደረጉ መከላከል እና እንክብካቤ የበለጠ ስኬታማ ሊሆኑ ይችላሉ-
- ልጆች፣ ቤተሰቦች፣ መምህራን እና ማህበረሰቦች በአይን እና ጆሮ ጤና አስፈላጊነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግርባራት ውስጥ ይካተታሉ።
- የሪፈራል አስፈላጊነት ከታወቀ ቤተሰቦች በፍጥነት ከዓይን ወይም ከጆሮ እንክብካቤ ሰራተኞች ጋር ቀጠሮ ማግኘት ይችላሉ። አፋጣኝ ህክምና ችግሮች እየባሱ እንዳይሄዱ ያደርጋል።