ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
መስማት

ለጆሮ ጤና ችግሮች የተለመዱ ምክንያቶች

ትምህርት፡- 2 የ 5
ርዕስ፡- 3 የ 3
0% ተጠናቋል

መመሪያ

በዚህ ርዕስ ውስጥ ስለ ጆሮ ጤና ችግሮች በጣም የተለመዱ መንስኤዎች ይማራሉ። 

የጆሮ ጤና ችግሮች መንስኤዎች

  1. የተደፈነ ጆሮ
  2. የጆሮ ኢንፌክሽን
  3. የአኗኗር ዘይቤ እና የአካባቢ አደጋዎች። 

የተደፈነ ጆሮ

የተደፈኑ ጆሮዎች ጊዜያዊ የመስማት ችግር ሊያስከትሉ ይችላሉ።

በተከማቸ የጆሮ ሰም ወይም በባዕድ አካል የሰው ጆሮ ሊደፈን ይችላል።

የጆሮ ሰም

የጆሮ ቦይ ቢጫ ወይም ቡናማ ሰም ያመነጫል፤ ይህም ጆሮን ለመከላከል ይረዳል። አዲስ ሰም ሲፈጠር አሮጌ ሰም በተፈጥሮ ከጆሮ ይወጣል። እሱን ማጽዳት አያስፈልግም።

አንዳንድ ጊዜ ሰም በጆሮ ውስጥ ይከማቻል። ይህ የጆሮውን ቦይ ሊዘጋ ይችላል። የጆሮ ሰም የጆሮ ቦይን በሚዘጋበት ጊዜ ደህንነቱን በጠበቀ ሁኔታ መወገድ አለበት።

ባዕድ አካል በጆሮ ውስጥ

ይህ የማይፈለግ ነገር ሲሆን በጆሮ ላይ ይጣበቃል ግን እዚያ መሆን የለበትም። 

በጆሮው ውስጥ ያለ ባዕድ አካል ደህንነቱን በጠበቀ ሁኔታ መወገድ አለበት። 

ጥያቄ

ስለ ጆሮ ሰም ከተናገሩት መግለጫዎች ውስጥ የትኛው ትክክል ነው?

ሶስቱን ይምረጡ።




ለ፣ ሐ እና መ ከመረጡ ትክክል ነዎት!

ሀ ትክክል አይደለም። የጆሮ ሰም የተለመደ ነው እና ብዙውን ጊዜ ከጆሮው ቦይ በራሱ ይወጣል። መወገድ ያለበት የጆሮ ሰም ሲከማች እና የጆሮ ቦይ ሲዘጋ ብቻ ነው።

የጆሮ ሰም ወይም የባዕድ አካላት በጆሮ እንክብካቤ ሰራተኞች መወገድ አለባቸው። አንድ ሰው ጆሮውን የሚዘጋውን ነገር በራሱ ለማንሳት ቢሞክር ጉዳዩን ሊያባብሰው እና ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።

የጆሮ ሰም የጆሮ ቦይን ይዘጋል።

የጆሮ ኢንፌክሽን

የጆሮ ኢንፌክሽን ጊዜያዊ የመስማት ችግርን ሊያስከትል ይችላል።

  • አብዛኛዎቹ ኢንፌክሽኖች ቀላል ህክምና ብቻ ያስፈልጋቸዋል
  • አንዳንድ ጊዜ ቀዶ ጥገና ያስፈልጋቸዋል።

አንዳንድ የጆሮ ኢንፌክሽኖች ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ ናቸው። ምንም ምቾት የሚነሳ ነገር ወይም ፈሳሽ ላይኖር ይችላል፤ ነገር ግን ኢንፌክሽኑ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል። 

ብቸኛው የችግር ምልክት የመስማት እክል ሊሆን ይችላል። ይህ ካልታከመ የልጁን ትምህርት ሊጎዳ ይችላል።

ካልታከመ የጆሮ ኢንፌክሽን የልጁን ታምቡር እንዲፈነዳ ሊያደርግ ይችላል፤ ይህም በጆሮ ላይ ዘላቂ ጉዳት ያስከትላል።

የአኗኗር ዘይቤ እና የአካባቢ አደጋዎች

በአኗኗራችን እና በአካባቢያችን ያሉ ነገሮች ለመስማት እና ለጆሮ ጤና ችግሮች ሊያጋልጡን ይችላሉ።

ጋሬትን አስታውስ?

የጋርሬት ምስል። ረዥም የተጠማዘዘ ፀጉር አለው። 

ጋሬት የ9 አመት ልጅ ሲሆን በአሳ ማጥመጃ መንደር ውስጥ ይኖራል። ከጓደኞቹ ጋር በባህር ውስጥ መዋኘት ይወዳል። ጋሬት ብዙ ጊዜ በጆሮው ላይ ህመም እና ፈሳሽ አጋጥሞታል። 

ጋሬት በቆሻሻ ውሃ ውስጥ ይዋኛል ስለዚህ ለጆሮ ኢንፌክሽን የመጋለጥ እድልቸው ከፈተኛ ከሆኑ ልጆች መካከል ነው።

መመሪያ

ለጤናማ አይን እና ጆሮ ጠቃሚ ምክሮች ስለ የአኗኗር ዘይቤ እና የአካባቢ አደጋዎች የበለጠ ይረዱ።

ትምህርት ሁለትን ጨርሰሃል!

0%
ለጆሮ ጤና ችግሮች የተለመዱ ምክንያቶች
ትምህርት፡- 2 የ 5
ርዕስ፡- 3 የ 3