ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
0% ተጠናቋል

የማጣሪያ ምርመራ ቅጽ

የማጣሪያ ምርመራ ቅጹ ለእያንዳንዱ ልጅ የስሜት ህዋሳትን ማጣሪያ ምርመራ እንዲያደርጉ እና እቅድ ለማውጣት ይረዳችኋል።

ልጁ ከዚህ ቀደም የእይታ እና የዓይን ጤና ማጣሪያ ምርመራ ካጠናቀቀ፤ ቅጹን ይዘው ይመጣሉ። 

መመሪያ

እስካሁን ካላደረጉት፣  የማጣሪያ ምርመራ ቅጹን ያውርዱ እና ቅጂ ያትሙ።

ቅጹን ማውረድ ካልቻሉ አይጨነቁ። በዚህ የሞጁሉ ክፍል ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ በቅጹ ላይ ያሉ ጥያቄዎች ይታያሉ።

የሚከተለው መመዝገቡን ያረጋግጡ፡-

  • የመርማሪው ስም (ከአንድ በላይ መርማሪ ከሆነ ሁለቱንም ስሞች ይጨምሩ)
  • የስክሪን ቀን
  • ማጣራት የሚካሄድበት ቦታ።

ስለ ልጁ መረጃ

ይፈትሹ፡

  • ስለ ልጁ መረጃ የያዘው ክፍል ተጠናቅቋል
  • በማጣሪያ ምርመራው ላይ ለመሳተፍ ከወላጆቻቸው/አሳዳጊዎቻቸው ፈቃድ ማግኘታቸውን ያረጋግጡ።

ፈቃድ ከተሰጠ ብቻ ይቀጥሉ።

የቅድመ ማጣሪያምርመራ ጥያቄዎች

ከማጣሪያ ምርመራው በፊት የወጡ ጥያቄዎች መረጃ ከፈቃድ ቅጹ የተወሰዱ መሆናቸውን አረጋግጥ።

መመሪያ

የሚከተለው ከሆነ ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለቦት እውቀትዎን ይፈትሹ፡-

  • አንድ ልጅ ቀድሞውኑ የመስሚያ አጋዦችን ይጠቀማል ወይም
  • ወላጅ/ተንከባካቢ ስለልጃቸው የመስማት ችግር ያሳስባቸዋል

የሚከተሉትን ጥያቄዎች በመመለስ።

ጥያቄ

ከባሲር ጋር ተገናኙ

ባሲር የስድስት አመት ልጅ ሲሆን የመስሚያ አጋዥ መሳሪያዎችን ለብሷል። በትምህርት ቤት ውስጥ በስሜት ህዋሳት ማጣሪያ ምርመራ ፕሮግራም ውስጥ እየተሳተፈ ነው።

ባሲር የመስማት እና የጆሮ ጤና ማጣሪያ ምርመራ ሲያካሂድ የመስሚያ አጋዦቹን አይለብስም። በማጣሪያ ምርመራ መጨረሻ ላይ ባሲር የመስማት ማጣሪያውን አያልፍም። ሁለቱም ጆሮዎቹ ጤናማ ናቸው።

1. የባሲርን ወላጆች ስታሳውቅ ባሲር እየተጠቀመበት ባለው አገልግሎት የጆሮ ተንከባካቢ ሰራተኞች እንዲከታተሉት ልትመክሩት ይገባል።

ይህ ምክር ትክክል ነው?


አዎ ልክ ነው!

ባሲር አስቀድሞ የመስሚያ አጋዦች አሉት። የመስሚያ አጋዥ መሳሪያዎችን በደንብ እየሰራ መሆኑን ለማረጋገጥ ቀደም ሲል በሚጠቀምበት አገልግሎት ክትትል መደረግ አለበት።

2. ወላጅ/ተንከባካቢ ስለልጃቸው የመስማት ችግር ስጋት ካለባቸው የማጣሪያ ምርመራውን ማጠናቀቅ አለቦት?


አዎ ልክ ነው!

የማጣሪያ ምርመራውን ማጠናቀቅ አስፈላጊ ነው።

ልጁ ማጣሪያውን ካለፈ ውጤቱን ከወላጅ/ተንከባካቢ ጋር ይወያዩ። በአንድ ወር ውስጥ የክትትል ማጣሪያ ምርመራ ያቅዱ።

ልጁ ማጣሪያውን  ካላለፈ ወደ ጆሮ እንክብካቤ ባለሙያዎችን ሪፈር ያድርጉ። 

0%
ስለ ልጁ መረጃ
ትምህርት፡- 4 የ 5
ርዕስ፡- 1 የ 4