ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
0% ተጠናቋል

መመሪያ

በዚህ ሞጁል ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ አንዳንድ ቁልፍ ቃላት ከዚህ በታች ተብራርተዋል። በሞጁሉን ሲያነቡ ለመጠቀም እነዚህን ማተም ይችላሉ፡-

ኦዲዮሜትር - የመስማት ችሎታን መመርመሪያ መሳሪያ ሲሆን መስማት ችሎታ ለመለካት ያገለግላል።

የመስማት ችሎታ መመርመሪያ መሳሪያ ከደወሎች፣ አዝራሮች እና ሄድፎኖች ጋር ተያይዟል። አንድ የሄድፎን ለቀኝ ጆሮ ቀይ ሲሆን አንዱ ሄድፎን ለግራ ጆሮ ሰማያዊ ነው። 

ኦዲዮሜትሪ - አንድ ሰው የጆሮ ማዳመጫዎችን በመልበስ የተለያዩ ድምፆችን የሚያዳምጥበት ምርመራ ሲሆን ምን ያህል መስማት እንደሚችል ለማረጋገጥ ነው። ማንኛውም የመስማት ችግር ካለ ውጤቶቹ በምን ያህል ደረጃ እንደሆነ ያሳያሉ። 

አንድ ሰው የጆሮ ማዳመጫዎችን ይጠቀማል። ሰውዬው እጁን ወደ ላይ አውጥቷል። አንድ የጤና ሰራተኛ ታብሌት ኦዲዮሜትር ከያዘው ሰው ጀርባ ቆሟል።

ታምቡር (ቲምፓኒክ ሽፋን) - ውጫዊውን እና መካከለኛውን ጆሮ የሚለይ እና መሃከለኛውን ጆሮ ከበሽታ የሚከላከል ቀጭን የቲሹ ሽፋን ነው። 

የጆሮው ቱቦ ወደ ታምቡር (ቲምፓኒክ ሽፋን) ይመራል። ታምቡር ውጫዊውን እና መካከለኛውን ጆሮ ይለያል።

የውጭ አካል - በሰውነት አካል ውስጥ የተጣበቀ የማይፈለግ ነገር ግን እዚያ መሆን የሌለበት። ለምሳሌ ከዓይኑ ክዳን በታች የሆነ የአሸዋ ቅንጣት ወይም በጆሮው ውስጥ ያለው ነፍሳት።

በሰው ጆሮ ቱቦ ውስጥ ያሉ ነፍሳት።

ድግግሞሽ - ድግግሞሽ የድምፅ ሞገድ በአንድ ሰከንድ ውስጥ ስንት ጊዜ ወደ ላይ እና ወደ ታች እንደሚንቀሳቀስ ነው። እንደ ከበሮ ያሉ ጥልቅ ድምፆችን (ዝቅተኛ ድግግሞሽ)  እና እና ሹል ድምፆች (ከፍተኛ ተደጋጋሚነት) እንደ ፉጨት ያሉትን ጨምሮ የተለያዩ አይነት የድምጽ አይነቶች አሉ። ድግግሞሽ የሚለካው በ Hertz (Hz) ይለካል።

የመስሚያ አጋዥ - የመስማት ችግር ያለባቸው ሰዎች በጆሮአቸው ላይ የሚለብሱት መሳሪያ ነው።  የመስማት አጋዦች አንዳንድ ድምፆችን ከፍ ያደርጋሉ፤ ይህም የመስማት ችግር ያለበት ሰው እንዲያዳምጥ፣ እንዲግባባ እና በእለት ተእለት እንቅስቃሴዎች ውስጥ የበለጠ እንዲሳተፍ ያደርገዋል።

የመስሚያ አጋዥ የፕላስቲክ መያዣ እና የጆሮ መንጠቆ አለው፤ ጆሮ ውስጥ ከሚገባ ማዳመጫ(ear mould) ጋር ተያይዞ።

ኦቶስኮፕ - የሰውን ጆሮ በእይታ ለመመርመር የሚያገለግል መብራት ያለው ማጉሊያ መሳሪያ።

ኦቶስኮፕ በአንደኛው ጫፍ እጀታ ያለው እና በሌላኛው ጫፍ ላይ ሹል ስፔኩለም እና የሚያበራ ባትሪ አለው።

ሰራተኛ - በአገልግሎት ወይም ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ናቸው። በልዩ ከጤና ጋር በተገናኘ የትምህርት ዘርፍ ሥልጠና የወሰዱ ሰዎችን ያጠቃልላል፤ እነሱም ሙያዊ ብቃት ላይኖራቸው ይችላል።

ስፔኩለም (Speculum) - ወደ ሰውየው ጆሮ ውስጥ የሚገባ የኦቶስኮፕ ተንቀሳቃሽ ጫፍ።

ሶስት የፕላስቲክ ኮኖች። ሰፊ ጫፍ ከኦቶስኮፕ ጋር ተያይዟል። ጠባብ ጫፍ በሰው ጆሮ ቱቦ ውስጥ መግባት እንዲችል ሦስት የተለያየ መጠን ያለው ቀዳዳ።

መመሪያ

የማታውቋቸው ሌሎች ቃላት ካገኙ የስራ ባልደረባዎን ወይም አማካሪዎን ይጠይቁ።

0%
ቁልፍ ቃላት
ትምህርት፡- 1 የ 5
ርዕስ፡- 1 የ 2