ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
መስማት

ጤናማ ጆሮዎች ምን እንደሚመስሉ

ትምህርት፡- 2 የ 5
ርዕስ፡- 1 የ 3
0% ተጠናቋል

መመሪያ

በዚህ ርዕስ ውስጥ ጤናማ ጆሮዎች ምን እንደሚመስሉ እና የጆሮ ጤና ችግሮች ምልክቶችን ይማራሉ።

እንደ የስሜት ህዋሳት ማጣሪያ ምርመራ ጤናማ እና ጤናማ ያልሆኑ ጆሮዎች ምን እንደሚመስሉ ማወቅ አስፈላጊ ነው።

የጆሮ ክፍሎች

ሶስት የጆሮ ክፍሎች አሉ፦

  1. ውጫዊ ጆሮ
  2. መካከለኛ ጆሮ
  3. የውስጥ ጆሮ

ውጫዊ ጆሮ

የውጪው ጆሮ በሚከተሉት ነገሮች የተሠራ ነው፦

  • ፒና
  • የጆሮ ቦይ
  • ትራገስ።

ትራገስ ወደ ጆሮ ቦይ መግቢያ ላይ ነው።

የጆሮ ቦይ ውጫዊውን እና መካከለኛውን ጆሮ ያገናኛል።

መካከለኛ ጆሮ

የመካከለኛው ጆሮው የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦

  • የጆሮ ታምቡር (ታይምፓኒክ ሽፋን)
  • ትናንሽ የመስማት አጥንቶች።

የጆሮ ታምቡር ውጫዊውን እና መካከለኛውን ጆሮ ይለያል። 

ሃሳብ

መካከለኛው ጆሮ ከአፍንጫው ጀርባ ጋር በቧንቧ ተያይዟል። ጉንፋን ካለብዎ የመደፈን ስሜት ሊሰማዎት እና በጆሮዎ ላይ ህመም ሊሰማዎት ይችላል.

  • ጉንፋን ሲይዞት በአንዱ ወይም በሁለቱም ጆሮዎ ላይ እንደተደፈነ ተሰምቶዎት ያውቃል?
  • በጆሮዎ ላይ ህመም ይሰማዎታል?

የውስጥ ጆሮ

የውስጣዊው ጆሮ ድምጽን ወደ ኤሌክትሪክ ሲግናሎች ይለውጣል፤ ይህም ከመስማት ነርቭ ወደ አንጎል ይጓዛል።

በማጣሪያ ምርመራ ጊዜ የውስጣዊውን ጆሮ ማየት አልተቻለም።

ጤናማ ጆሮዎች

ጤናማ ውጫዊ ጆሮዎች (ፒና) በትንሹ የተለያየ ቅርጾች እና መጠኖች ናቸው። ሁሉም ጤናማ ጆሮዎች የጆሮ ቦይ አላቸው።

መመሪያ

እነዚህን ጤናማ የፒና ምሳሌዎችን ተመልከት።

ምንም ምልክቶች የሉም፦

  • ጉዳት /ቁስል
  • እብጠት
  • በቀለም ለውጥ (ቀይ/ሐምራዊ)
  • መፍሰስ (ደም ፣ መግል ፣ ፈሳሽ)።

የአንድ ሰው የፒና ወይም የጆሮ ቦይ ከጠፋ ወይም በጣም የተለያየ ቅርጽ ካለው ግለሰቡ የበለጠ ውስብስብ ፍላጎቶች አሉት እና   ወደ ጆሮ እና የመስማት ባለሙያ ሪፈር መደረግ አለበት። 

ጤናማ ጆሮዎች ምንም እንደዚህ አየነት ምልክቶች የላቸውም፦

  • ኢንፌክሽን
  • የተደፈነ ጆሮ።

የጆሮ ታምቡር እንደሚከተለው መሆን አለበት፦

  • ግልጽ(በከፊል የሚያሳይ )
  • ነጭ / ቀላል ግራጫ ቀለም
  • ምንም ቀዳዳዎች የሉም።

የአንድ ሰው ጤናማ የጆሮ ቦይ እና ታምቡር።

0%
ጤናማ ጆሮዎች ምን እንደሚመስሉ
ትምህርት፡- 2 የ 5
ርዕስ፡- 1 የ 3