ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
መስማት

የተካተቱ የመስማት ረዳት ምርቶች

ትምህርት፡- 2 የ 5
ርዕስ፡- 1 የ 2
0% ተጠናቋል

የመስማት ረዳት ምርቶች  የመስማት ችግር ያለባቸው በሁሉም ዕድሜ ላይ ያሉ ሰዎች ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

አንዳንድ በብዛት ጥቅም ላይ የዋሉ የመስማት ረዳት ምርቶች እንዚህን ያካትታሉ፦

  • የመስሚት አጋዦች
  • የግል የርቀት ማይክሮፎን ስርዓቶች(Personal remote microphone systems)።

መመሪያ

ስለ እነዚህ ምርቶች መግለጫ ለማግኘት ማንበብዎን ይቀጥሉ። 

የመስሚት አጋዦች

የመስሚያ አጋዦች በጆሮ ላይ የሚለበሱ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ናቸው። አንድ ሰውን በተሻለ ሁኔታ መስማት እንዲችል አንዳንድ ድምፆችን ከፍ በማድረግ አንድን ሰው ይረዳሉ።

ከጆሮው ጀርባ የመስማት አጋዦች

እነዚህ የመስሚያ አጋዦች ከሰው የጆሮ ጀርባ ይገጠማሉ።

ሁለት አይነት ከጆሮ ጀርባ የመስማት አጋዥ መሳሪያዎች ተካትተዋል፡-

1. በቅድሚያ ፕሮግራም የተደረጉ የመስሚያ አጋዦች 

እነዚህ ቀደም ሲል በተለመደው የመስማት ችግር ዓይነቶች መሰረት ፕሮግራም የተደረጉ ናቸው።  የፕሮግራሞችን ወይም ቅንብሮችን በእጅ ማስተካከል ብቻ ነው የሚጠይቁት።

በቅድሚያ ፕሮግራም የተደረጉ የመስሚያ አጋዦች ለአዋቂዎች ብቻ ተስማሚ ናቸው።

መመሪያ

በTAP በቅድሚያ ፕሮግራም የተደረገ የመስሚያ አጋዥ ሞጁል ውስጥ ስለ በቅድሚያ ፕሮግራም የተደረገ የመስሚያ አጋዥ የበለጠ ይወቁ።

2. ፕሮግራም የሚደረጉ የመስሚያ አጋዦች

ሊስተካከል የሚችለው በ፦

  • የኮምፒውተር ሶፍትዌር
  • መተግበሪያ።

መመሪያ

በTAP በቅድሚያ ፕሮግራም የተደረገ የመስሚያ አጋዥ ሞጁል ውስጥ ስለ በቅድሚያ ፕሮግራም የተደረገ የመስሚያ አጋዥ የበለጠ ይወቁ።

ከሜሬ ጋር ተገናኙ

ሜሬ ወጣት ሴት ነች። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለች የመስማት ችግር ገጥሟታል። በእናቷ ፈቃድ፣ ሜሬ በአካባቢው ወደሚገኝ የመስማት አገልግሎት ሰጪ ሪፈር ተድርጋለች እና ዲጂታል የመስሚያ አጋዥ መሳሪያ ተገጥሞላታል።

የመስሚያ አጋዡ ፕሮግራም የተደረገው በጤና ሰራተኛው ለሜሬ ነው።

በዚህ ሞጁል ውስጥ ዲጂታል የመስሚያ አጋዞች ብቻ ተካትተዋል።

የግል የርቀት ማይክሮፎን ስርዓቶች(Personal remote microphone systems)

የግል የርቀት ማይክሮፎን ሲስተሞች(Personal remote microphone systems) የመስሚያ አጋዥ መሳሪያዎችን የሚጠቀሙ ሰዎች ጫጫ ታ በሚበዛባቸው እንደ ክፍሎች፣ የስራ ቦታዎች ወይም የአምልኮ ስፍራዎች የተሻለ እንዲሰሙ ይረዷቸዋል።

ከማህሙድ ጋር ተገናኙ

ማህሙድ 19 አመቱ ሲሆን በኮሌጅ እየተማረ ነው። በሁለቱም ጆሮዎች ላይ መጠነኛ ከባድ የመስማት ችግር አለበት እና የመስሚያ አጋዥ መሳሪያዎችን ይለብሳል።

ማህሙድ የመስሚያ አጋዥ መሳሪያዎችን ቢለብስም ትምህርቶችን መረዳት ይቸግራል።

የእሱ አገልግሎት አቅራቢው የርቀት ማይክሮፎን ስርዓት (remote microphone system)ሊረዳው እንደሚችል አስረድቷል።

በትምህርት ጊዜ ፕሮፌሰሩ የማይክሮፎን አስተላላፊ ይለብሳሉ። ይህ ከማህሙድ የመስሚያ አጋዥ መሳሪያ መቀበያ ጋር ይገናኛል።

ማህሙድ አሁን ፕሮፌሰሩን በትምህርት ጊዜ በግልፅ መስማት ይችላል።

መመሪያ

በTAP የግል የርቀት ማይክሮፎኖች(personal remote microphones) ሞጁል ውስጥ ስለግል የርቀት ማይክሮፎኖች(Personal remote microphones) የበለጠ ይወቁ።

0%
የተካተቱ የመስማት ረዳት ምርቶች
ትምህርት፡- 2 የ 5
ርዕስ፡- 1 የ 2