የግምገማ ደረጃዎች
የTAP የእይታ ምርመራ
አንድ ሰው በማንበቢያ መነጸር ተጠቃሚ መሆን አለመሆኑን ለመገምገም የመጀመሪያው ደረጃ የTAP እይታ ምርመራ(ወይም ተመሳሳይ የእይታ ምርመራ) መደረግ አለበት።
የእይታ ምርመራ የማንበቢያ መነፅር ሊረዳ እንደሚችል የሚያመለክት ከሆነ፤ ምን አይነት መጠን ለሰውዬው ተስማሚ እንደሚሆን ይገመግሙ።
ለአንድ ሰው የንባብ መነፅር መጠን የመወሰኛ ቀላል ዘዴን ለማየት ያንብቡ።
የትኛውን የንባብ መነፅር መጠን ለሰውየው እንደሚስማማ ይወስኑ
እንደ ሰውዬው ዕድሜ ጥንድ የንባብ መነጽር እንዲመክሩ ይምረጡ። ለአረጋዊ ሰው፦
- 35-44 - +1.00 ይምረጡ
- 45-50 - +1.50 ይምረጡ
- 51-55 - +2.00 ይምረጡ
- ከ 55 በላይ - +2.50 ይምረጡ
የቅርብ እያታን ኢ-ሰንጠርዥ በመጠቀም ሰውዬው ትንሹን Es ምን ያህል ማየት እንደሚችል ይፈትሹ። ኢ-ሰንጠርዡን ሰውየው በጣም ማየት ከሚያስፈልገው ቦታ ጋር በሚዛመድ ርቀት ይያዙ።
ሰውዬው Es በግልፅ ማየት ከቻለ ያንን ጠንካራ መጠን ይዝዙ።
ሰውዬው Es በግልፅ ማየት ካልቻለ የሚቀጥለውን ጠንካራ መጠን ወይም የሚቀጥለውን ደካማ ቁጥር ይሞክሩ። ሰውዬው ትንሹን Es በግልፅ ማየት እስኪችል ድረስ ይሞክሩት።
ሰውዬው ትንሹን Es በግልፅ እንዲያይ የሚረዳውን ጥንካሬ ማግኘት ካልተቻለ ለበለጠ ግምገማ ወደ የዓይን ጤና አጠባበቅ ባለሙያን ይላኩ።