ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
መስማት

የጆሮ ጤና

ትምህርት፡- 1 የ 5
ርዕስ፡- 4 የ 5
0% ተጠናቀቀ

መመሪያ

በዚህ ርዕስ ውስጥ ስለ ጆሮ ጤና ይማራሉ።

ጤናማ ጆሮዎች

በሁለቱም በኩል የአንድን ሰው ጆሮ ውጫዊ እና ውስጣዊ ሁኔታ መፈተሽ አስፈላጊ ነው።

ጤናማ ውጫዊ ጆሮዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • በጥቂቱ በተለያዩ ቅርጾች እና መጠኖች የሚመጣው ፒና
  • የጆሮ ቱቦ
  • የጉዳት ወይም የኢንፌክሽን ምልክቶች የሉም።
ፒና

መመሪያ

እነዚህን ጤናማ የፒና ምሳሌዎችን ተመልከት።

የአንድ ሰው የፒና ወይም የጆሮ ቱቦ ከጠፋ ወይም በጣም የተለያየ ቅርጽ ካለው ሰውዬው የበለጠ ውስብስብ ህክምና የሚፈልጉ ጉዳቶች አሉት። ወደ ጆሮ እና የመስማት ችሎታ ባለሙያ ሪፈር ያድርጉ።

ፒና፣ በጣም የተለያየ ቅርጽ

ጤናማ ያልሆኑ ጆሮዎች

የሰው ጆሮ ከተጎዳ ወይም ከተበከለ ጤናማ አይደለም። የኢንፌክሽን ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • እብጠት
  • በቀለም ለውጥ (ቀይ/ሐምራዊ)
  • ፍሳሽ (ደም ፣ መግል ፣ ፈሳሽ)።

ሁልጊዜ የሰውን ጆሮ ከፊት እና ከኋላ ይመልከቱ።

ጥያቄ

እነዚህን የጆሮ ውጫዊ ምስሎች ይመልከቱ። ጤናማ ይመስላሉ?

የጆሮው ፒና ያበጠ እና ቀይ ነው።

አይደለም። የዚህ ሰው ጆሮ የኢንፌክሽን ምልክቶች አሉት ከእብጠት እና የቀለም ለውጥ ጋር።

ጆሮው ያበጠ እና በፒና አናት ላይ ደም ይፈስሳል።

አይደለም። እንደ እብጠት እና የደም መፍሰስ የመሰሉ የጉዳት ምልክቶቸ አሉት።

ከጆሮው ጀርባ  እብጠት እና ቀለም ለውጥ ይታይበታል።

አይደለም። ከጆሮ ጀርባ የኢንፌክሽን ምልክቶች አሉ ከእብጠት እና የቀለም ለውጥ ጋር ።

ከጆሮው የሚወጣ ፈሳሽ አለ።

አይደለም። ከጆሮ የሚወጣ ፈሳሽ አለ።

ጆሮው ምንም ደም መፍሰስ፣ እብጠት ወይም መቅላት የለውም። የጆሮ ቱቦ ጤናማ ነው።

አዎ! የዚህ ሰው ጆሮ ጤናማ ነው። የጉዳት ወይም የኢንፌክሽን ምልክት አይታይም እና የጆሮው ቱቦ አለ።

ጆሮዎች ውስጥ

ኦቶኮስኮፕ በጆሮው ውስጥ ያለውን የጆሮ ችግር ለመመርመር ይረዳል። ኦቶስኮፕ በጆሮው ውስጥ ብርሃን የሚያበራ ማጉያ ነው።

መመሪያ

ኦቶስኮፕን እንዴት እንደሚጠቀሙ በክፍል ሶስት የበለጠ ይማራሉ ።

ወደ ጆሮው ውስጥ ሲመለከቱ ጤናማ ነው፦

  • የጆሮ ቱቦ ግልጽ ነው (አልተደፈነም)
  • የጆሮ ታምቡር፡-
    • ግልጽ(በከፊል የሚያሳይ)
    • ነጭ / ነጣ ያለ ግራጫ ቀለም
    • ቀዳዳዎች የሉትም።
  • የኢንፌክሽን ምልክቶች (እብጠት፣ ቀለም መቀየር፣ ፈሳሽ) አይታዩም።
ጤናማ የጆሮ ውስጠኛ ክፍል

ጥያቄ

እነዚህን የጆሮው ውስጣዊ ምስሎች ይመልከቱ። ጤናማ ይመስላሉ?

የጆሮው ታምቡር ሁለት ቀዳዳዎች ያሉት ሲሆን ቀይ እና ያበጠ ነው።

አይደለም። በታምቡር ውስጥ ሁለት ቀዳዳዎች አሉ፤ ቀይ እና ያበጡ ናቸው።

የጆሮው ቱቦ ቀይ ነው እና ሙሉ በሙሉ በእብጠት ተዘግቷል።

አይደለም። የጆሮ ቱቦ ቀይ እና ያበጠ ነው።

ባእድ አካል ጆሮው ቱቦ ውስጥ።

አይደለም። ባዕድ አካል በጆሮ ቱቦ ውስጥ አለ።

የጆሮው ቱቦ አልተደፈነም። የጆሮው ታምቡር ግልጽ እና ነጭ/ነጣ ያለ ግራጫ ቀለም ነው።

አዎ! የጆሮ ቱቦ ግልጽ ነው። የጆሮው ታምቡር ግልጽ እና ነጭ/ነጣ ያለ ግራጫ ቀለም ነው።