የስሜት ህዋሳት ማጣሪያ ምርመራ፣ የሰውን የአይን ውጫዊ ክፍል ብቻ ነው የሚፈትሹት።
የዓይን ጤና ችግሮች ምልክቶች
አንድ ልጅ የዓይን ጤና ችግር እንዳለበት የሚያሳዩ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
- በዐይን ሽፋሽፍት እና/ወይም ሽፋሽፍቶች ላይ ቅርፊት ወይም መግል
- ከዓይን የሚወጣ ፈሳሽ ወይም የሚያጣብቅ ፈሳሽ
- በነጭ የዓይን ክፍል ላይ ያልተለመደ ቀይ ቀለም
- ባለቀለም የዓይን ክፍል ግልጽ ያልሆነ ወይም 'ወተት ቀለም ያለው' ይመስላል
- አይን / ዎች እርስ በእርሳቸው በአንድ አቅጣጫ አያዩም።
መመሪያ
የዓይን ጤና ችግርን የሚያሳዩ የተለመዱ ምልክቶችን ዝርዝር ያንብቡ እና ተዛማጅ ምስሎችን ይመልከቱ።





ማስጠንቀቂያ
የዓይን ጤና ችግሮችን በጊዜ መለየት አስፈላጊ ነው። ሕክምና ካልተደረገለት የዓይን ጤና ችግሮች በአይን ላይ ዘላቂ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ይህ የእይታ ማጣት ሊያስከትል ይችላል።