ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
መግቢያ

ሰዎች በማህበረሰቡ ውስጥ አጋዥ ምርቶችን እንዲጠቀሙ መደገፍ

ትምህርት፡- 4 የ 5
ርዕስ፡- 2 የ 2
0 % ሙሉ

ለብዙ ሰዎች አጋዥ ምርቶችን ማግኘት በሚፈልጉት ወይም በሚያስፈልጋቸው ተግባራት ላይ መሳተፍ ለማስቻል አስፈላጊ ክፍል ነው።

በትክክለኛው የአጋዥ ምርትም ቢሆን እንኳን ሰዎች ተሳትፏቸውን የሚገድቡ ተግዳሮቶች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ።

እነዚህ ተግዳሮቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

  • ተደራሽ ያልሆነ አካባቢ
  • ማህበራዊ መገለል እና አድልዎ
  • የተደራሽ መረጃ እጥረት
  • የድጋፍ አገልግሎቶች ወይም ፖሊሲዎች እጥረት።

አጋዥ ምርቶችን የሚጠቀሙ ሰዎች በሚፈልጉት ወይም በሚያስፈልጋቸው ተግባራት ከሌሎች ጋር በእኩልነት እንዲሳተፉ ለማድረግ ሁሉም ሰው ሚና አለው።

ሌይ ሐምራዊ ቲሸርት ለብሳ ቆማለች። አንድ ክንድ ከጎኗ ሲኖራት ሌላኛው ደግሞ ወደ ሰውነቷ ታጥፏል።

ከሌይ ጋር ተገናኙ።

ሌይ ስትሮክ አጋጥሟታል የምትኖረውም ከልጇ ጋር ነው። የሌይ አካል የቀኝ ጎን ደካማ ነው እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ንግግሯ ግልጽ አይደለም። ለመራመድ እንዲረዳት ዘንግ ትጠቀማለች።

ከስትሮክ በፊት ሌይ በማህበረሰቡ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ነበረች እና ብዙ ጊዜ አትክልቶችን በአካባቢው ገበያ ትሸጥ ነበር። ሆኖም ከስትሮክ በኋላ ወደ ገበያ ለመሄድ ወደ አውቶቡሱ ለመግባት ተቸግራለች። በገበያው ላይ የነበሩ አንዳንድ ሴቶች እሷን በንግግራቸው እና በተግባራቸው ማካተት እንዳቆሙ አስተውላለች።

በገበያው አካባቢ አውቶቡስ ቆሟል። አንድ ሰው ለሁለት ሴቶች በሩን ከፈተላቸው አንደኛዋ ዘንግ ትጠቀማለች።

ሌይ ብቸኝነት ተሰማት እና ብዙ ጊዜ ወደ ገበያ አትሄድም። ሆኖም አንድ ቀን የአውቶቡስ ሹፌር የሰራውን ትንሽ ተንቀሳቃሽ ደረጃ ለሌይ አሳያት፤ ይህም ወደ አውቶቡሱ ለመውጣትና ለመውረድ በጣም ቀላል አድርጎላታል።

ሌይ እና ጓደኛዋ ከገበያ ድንኳናቸው ጀርባ አትክልት እየሸጡ ጎን ለጎን ቆመው ነበር።

በገበያ ላይ የምትገኝ የሌይ ጓደኛም ከሌሎች ሴቶች ጋር እንድትነጋገር ረዳቻት እና ሌይ አሁንም መረዳት እና በውይይት መሳተፍ እንደምትችል ነገር ግን በግልጽ ለመናገር ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልጋት አስረዳች። ሌሎቹ ሴቶች ተረድተው እሷን እንደገና በተግባሮቻቸው እና ንግግራቸው ውስጥ አካተቷት እናም ምላሽ ለመስጠት የምትፈልገውን ያህል ጊዜ ይሰጥዋታል።

ሌይ እንደገና አትክልቶቿን በገበያ ትሸጣለች እና ከሌሎች ሴቶች ጋር መነጋገር ትወዳለች።

ጥያቄ

1. ሌይ ከተሳትፎ ተግዳሮቶች ምን አጋጥሟት ነበር?

1. ሌይ ያጋጠማት፡-

  • የአካል ተግዳሮቶች (ወደ አውቶቡስ ለመግባት ከበዳት)
  • የአመለካከት ተግዳሮቶች (በገበያ ላይ ያሉ ሴቶች ሌይን ከንግግራቸው እና ከተግባራቸው አገለሉ)።

2. እንዴት ነው ማሸነፍ የቻለችው? የተለያዩ ሰዎች ምን ሚና ተጫውተዋል?

2. በማኅበረሰቧ ውስጥ ባሉ ሰዎች ድጋፍ ተግዳሮቶችን አሸንፋለች፡-

  • የአውቶቡስ ሹፌር ሌይ ከአውቶቡሱ እንድትወጣ እና እንድትወርድ ተንቀሳቃሽ ደረጃዎች(portable step) በማድረግ የአካል መሰናክሎችን እንድታሸንፍ ረድቷታል።
  • ሌይ አሁንም በንግግራቸው እና በተግባራቸው መሳተፍ እንደምትችል እንዲረዱ የሌይ ጓደኛ ከሌሎች ሴቶች ጋር እንድትነጋገር ደገፈቻት።

ትምህርት አራት ጨርሰሃል!