ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
መግቢያ

ሪፈራሎችን መስራት እና መከታተል

ትምህርት፡- 3 የ 4
ርዕስ፡- 1 የ 1
0% ተጠናቋል

መመሪያ

በዚህ ርዕስ ውስጥ ስለ ሪፈራሎች እና ለምን እነሱን መከታተል አስፈላጊ እንደሆነ ይማራሉ።

ወላጆችን/ተንከባካቢዎችን ማነጋገር

አንድ ልጅ ወደ ዓይን እና/ወይም የጆሮ እንክብካቤ ሰራተኞች ሪፈር መደረግ የሚያስፈልገው ከሆነ፤ ትምህርት ቤቱ ይህንን ለወላጆች/ተንከባካቢዎች ያብራራል።

ወላጆች/ተንከባካቢዎች የማሳወቂያ ቅጽ በመጠቀም ልጃቸውን የት እንደሚወስዱ መረጃ ይሰጣቸዋል።

ለምንድነው ሪፈራልን መከታተል አስፈላጊ የሆነው?

የማጣሪያ ምርመራ ፕሮግራሙ ዋና አላማ ወደ ዓይን እና/ወይም የጆሮ እንክብካቤ ሰራተኞች ሪፈራል የሚያስፈልጋቸውን ልጆች መለየት ነው።

ነገር ግን ልጆች ሪፈር ወደ ተደረጉባቸው አገልግሎቶች ላይወሰዱ ይችላሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ፕሮግራሙ ስኬታማ አልሆነም።

በሚያሳዝን ሁኔታ የሚያስከትለው ውጤቶቹ ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ።

አስፈላጊ ነው፦

  • በክትትል ቀጠሮዎች ላይ መገኘትን ይከታተሉ
  • እነሱን ለማበረታታት እና ልጆቻቸውን ወደ ሪፈራል ቀጠሮ የሚወስዱበትን መንገድ ለማመቻቸት ከወላጆች/አሳዳጊዎች ጋር ይገናኙ።

የሪፈራል ዝርዝር ይከታተሉ

የክትትል ሪፈራል ዝርዝሩ መርማሪው እና ትምህርት ቤቱ ሪፈር የተደረጉ ልጆችን እንዲከታተሉ ይረዳል።

  • ሪፈር የተደረጉ ልጆች በጆሮ ወይም በአይን ተንከባካቢዎች መታየታቸውን ለመከታተል የክትትል ሪፈራል ዝርዝሩን ይጠቀሙ
  • ልጆች በቀጠሮ ካልተገኙ ምክንያቱን ለመረዳት የትምህርት ቤቱ የማጣሪያ ምርመራ አስተባባሪ ከወላጆች/አሳዳጊዎች ጋር መገናኘት ወይም መነጋገር ይችላል።

ጀባሪን አስታውስ?

ጀባሪ (የትምህርት ቤት ማጣሪያ ምርመራ አስተባባሪ) ለክትትል ቀጠሮአቸው ስላልተገኘ ልጅ መልእክት ደረሰው።

ጀባሪ ለቤተሰቡ ይደውላል። ከሥራ ዕረፍት ስለማግኘት እንደሚጨነቁ ተገነዝቦል። ጃባሪ ሪፈር የተደረጉበት የአይን ህክምና አገልግሎት የማታ ቀጠሮ እንደሚሰጥ ሊያረጋግጥላቸው ችሏል።

ትምህርት ሶስትን ጨርሰሃል!

0%
ሪፈራሎችን መስራት እና መከታተል
ትምህርት፡- 3 የ 4
ርዕስ፡- 1 የ 1