ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
መስማት

የጆሮ ጤና ምርመራ

ትምህርት፡- 3 የ 5
ርዕስ፡- 5 የ 5
0% ተጠናቀቀ

የTAP የጆሮ የጤና ማጣሪያ ምርመራ ሶስተኛው ክፍል የጆሮ ጤና ምርመራ ነው።

አንድ ሰው ከመስማት ረዳት ምርቶች ሊጠቀም ይችል እንደሆነ ለመገምገም የመስማት ችሎታ ምርመራ ከማጠናቀቅዎ በፊት የግለሰቡ ጆሮ ጤናማ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

የጆሮው ውጫዊ ክፍል ይመርምሩ

መመሪያ

ያረጋግጡ ፡ ሁለቱም ጆሮዎች ጤናማ ይመስላሉ?

የኦቶስኮፕ ብርሃን በመጠቀም የግለሰቡን ውጫዊ ክፍል በቅርበት በመመልከት ይጀምሩ።

በእያንዳንዱ ጎን የፒናናቸውን ፊት እና ጀርባ ይመልከቱ። እንዚህ ነገሮች መኖራቸውን ይፈትሹ፦

  • የጉዳት ወይም የኢንፌክሽን ምልክቶች
  • የጆሮ ቦይ መኖር።

ጥያቄ

የዚህን ሰው ፒና ተመልከት።

የግለሰቡ ፒና ምንም የጆሮ ቱቦ የለውም፤ የተለየ ቅርጽ አለው።

1. ጆሮአቸውን ከተመለከቱ በኋላ ምን እርምጃ ይወስዳሉ?

አንዱን ይምረጡ።


የጆሮ ጤና ማጣሪያ ምርመራን ያቁሙ። የዚህ ሰው ጆሮ የጆሮ ቦይ የለውም። የበለጠ ውስብስብ ፍላጎቶች አሏቸው። በነሱ ፍቃድ በአካባቢ ወደሚገኘው የጆሮ እና የመስማት ባለሙያን ሪፈር ያድርጉ።

2. የመጎዳት ወይም የኢንፌክሽን ምልክቶች በፒና ላይ ካዩ ምን ያደርጋሉ?

አንዱን ይምረጡ።


የጆሮ ጤና ማጣሪያ ምርመራን ያቁሙ። የዚህ ሰው ጆሮ ጤናማ አይደለም። በነሱ ፍቃድ ለህክምና በአካባቢ ወደሚገኘው የጆሮ እና የመስማት ባለሙያን ሪፈር ያድርጉ። ከህክምናው በኋላ ለጆሮ ጤና ማጣሪያ ምርመራ እንዲመለሱ ይጠይቋቸው።

የጆሮውን ውስጣዊ ሁኔታ ይፈትሹ

እያንዳንዱን ጆሮ በኦቶስኮፕ በጥንቃቄ ይመልከቱ።

መመሪያ

እነዚህን ነገሮች ካሉ ይፈትሹ፦

  • የጆሮ ፈሳሽ ወይም ኢንፌክሽን
  • ጆሮ በጆሮ ሰም ተደፍኖል
  • ባዕድ አካል በጆሮ ውስጥ
  • በጆሮ ታምቡር ውስጥ ያለው ቀዳዳ።

የጆሮ መፍሰስ (ደም ፣ ፈሳሽ ፣ ፈሳሽ)

ምንም አይነት ፈሳሽ ካለ ኦቶኮስኮፕን ከመጠቀምዎ በፊት ያጽዱት።

  • የግለሰቡ የጆሮ ቦይ እና ታምቡር ጤናማ የሚመስሉ ከሆነ ምርመራውን ይቀጥሉ።
  • የግለሰቡ የጆሮ ቱቦ እና ታምቡር ጤነኛ ካልሆነ በፈቃዱ ለህክምና ወደ ጆሮ እና የመስማት ባለሙያ ሪፈር ያድርጉ። ህክምና ካገኘ በኋላ ለጆሮ ጤና ልየታ እንዲመለስ ይንገሩት።

ጥያቄ

ከቤን ጋር ተገናኙ

ቤን 64 ዓመቱ ነው። ከጓደኞቹ ጋር ለቡና መገናኘት ያስደስተዋል። በቅርቡ ቤን መጥፎ ጉንፋን እና ትኩሳት ነበረው። አሁን በግራ ጆሮው ላይ ህመም እና ፈሳሽ እያጋጠመው ነው።

የጆሮውን ውስጠኛ ክፍል መመርመር እንደሚፈልጉ ለቤን ያስረዱት።

1. መጀመሪያ ምን ታደርጋለህ?

አንዱን ይምረጡ።



በደረቅ ጨርቅ ጆሮውን ማጽዳት ትክክል ነው!

የቤን ጆሮ ፈሳሽ አለው። ጆሮውን በኦቶስኮፕ ከመመልከትዎ በፊት ፈሳሹን በደረቅ ጨርቅ ማጽዳት አስፈላጊ ነው።

የቤን የግራ ጆሮ ውስጠኛ ክፍል ሲመለከቱ በኦቶስኮፕ በኩል የሚያዩትን ምስል ይመልከቱ።

የቤን የግራ ጆሮ ቱቦ እና ታምቡር ቀይ እና ጎበጥ ያለ ነው።

2. የቤን ግራ ጆሮ ውስጠኛው ክፍል ጤናማ ይመስላል?

አንዱን ይምረጡ።


አይ ልክ ነው!

የቤን ግራ ጆሮ ጤናማ አይመስልም። የጆሮው ታምቡር ቀይ እና ጎበጥ ያለ ነው።

በተጨማሪም የቤን ቀኝ ጆሮን መመርመር አስፈላጊ ነው። 

3. ለቤን ምን እርምጃ ትመክራለህ?

ሁለቱን ይምረጡ።




ሀ እና መ ከመረጡ ትክክል ነዎት!

ቤን ለጆሮው ኢንፌክሽን ሕክምና ቢደረግለት ተጠቃሚ ይሆኖል። ከህክምናው በኋላ ቤን ጆሮው ጤናማ መሆኑን ለማረጋገጥ ለተደጋጋሚ የጆሮ ጤና ልየታ መምጣት አለበት።

ለ እና ሐ የተሳሳቱ ናቸው!

ቤን የመስማያ አጋዥ ቢያደርግ ተጠቃሚ እንደሚሆን ለማረጋገጥ ወደ ጆሮ ምርመራ ከመቀጠላችን በፊት ሁለቱም ጆሮዎች ጤናማ መሆን አለባቸው። 

ጆሮ በጆሮ ሰም ተደፍኖል

የጆሮውን ታምቡር ሙሉ በሙሉ ማየት ካልቻሉ ምናልባት ሰም እንዳይታይ እየከለከለው ሊሆን ይችላል።

ብዙ ሰም ካለ በማጠብ ያስወግዱት እና የጆሮ ምርመራውን ይቀጥሉ።

ሰሙን በማጠብ ካልተወገደ፤ ግለሰቡ ፈቃደኛ ከሆነ ወደ ጆሮ እና የመስማት ባለሙያ ሪፈር ያድርጉ።

የግለሰቡ የጆሮ ቱቦ በቢጫ እና ቡናማ ጆሮ ሰም ተዘግቷል።
ጆሮ በሰም ተደፍኖል

ጥያቄ

የጆሮ ሰም ካስወገዱ በኋላ ምን ማድረግ አለብዎት?

አንዱን ይምረጡ።



ለ  ከመረጡ ትክክል ነዎት!

የጆሮው ቦይ በግልጽ የሚታይ መሆኑን እና ታምቡር ጤናማ መሆኑን ለማረጋገጥ የግለሰቡን የጆሮ ውስጠኛ ክፍል ማየት አስፈላጊ ነው። ጆሮአቸው ጤናማ ከሆነ፤ የመስማት ምርመራ ለማድረግ ያቅዱ።

ሀ እና ሐ የተሳሳቱ ናቸው።

በደረቅ ጨርቅ ማጽዳት የሚያስፈልገው ግለሰቡ የጆሮ ፈሳሽ ካለበት ብቻ ነው።

ባዕድ አካል በጆሮ ውስጥ

በጆሮው ውስጥ ባእድ አካል ካዩ፤ በጆሮ አጠባ ያስወግዱት እና የጆሮ ምርመራን ይቀጥሉ።

ጆሮው ከታጠበ በኋላ ባእድ አካሉ አሁንም ካለ በግለሰቡ ፍቃድ ወደ ጆሮ እና የመስማት ባለሙያ ሪፈር ያድርጉ። 

በጆሮ ቱቦ ውስጥ የውጭ አካል

በጆሮ ታምቡር ውስጥ ያለው ቀዳዳ

አንድ ሰው በጆሮው ውስጥ ቀዳዳ ካለው ወደ ጆሮ እና የመስማት ችሎታ ባለሙያ ሪፈር ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል።

የጆሮው ታምቡር ሁለት ቀዳዳዎች ያሉት ሲሆን ቀይ እና ያበጠ ነው።
በጆሮ ታምቡር ውስጥ ያሉ ቀዳዳዎች

ጥያቄ

የግለሰቡን የጆሮ ታምቡር ለማየት ከተቸገሩ ምን ማድረግ ይችላሉ?

ሁለቱን ይምረጡ።



ሀ እና ሐ ከመረጡ ትክክል ነዎት!

የኦቶስኮፕ ብርሃን እና አቅጣጫ በግለሰቡ ጆሮ ውስጥ በግልጽ ለማየት አስፈላጊ ናቸው።

ለ ትክክል አይደለም።

ጆሮውን በደንብ ለማየት የጆሮ አጠባ ጥቅም ላይ አይውልም። የጆሮ ሰም እና የውጭ አካላትን ለማስወገድ ያገለግላል።

ጤናማ / ምንም የጆሮ ችግር የለም

ሁለቱም ጆሮዎች ጤናማ የሚመስሉ ከሆነ የመስማት ችሎታ ምርመራ ለማድረግ እቅድ ማውጣት እንደሚችሉ ለግለሰቡ ያስረዱ።

ተግባር

የአንድን ሰው ግራ እና ቀኝ ጆሮ ምስሎች ይመልከቱ እና በልየታ ቅጹ ላይ ያለውን የጆሮ ምርመራ ክፍል ይሙሉ።

የግራ ጆሮ፦

የአንድ ሰው ግራ ፒና ኢንፌክሽን አለው እና ያበጠ ነው።

የቀኝ ጆሮ፦

የአንድ ሰው የቀኝ ፒና ነጣ ያለ የቀይ ቀለም አለው፤ ጤናማ ነው።

1. ሁለቱም ጆሮዎች ጤናማ ይመስላሉ?

አንዱን ይምረጡ።


አይ ልክ ነው!

የግራ ጆሮው የኢንፌክሽን ምልክቶች አሉት።  የቀኙ ጆሮ ጤናማ ነው።

2. ምን እርምጃዎችን ይወስዳሉ?

ሁለቱን ይምረጡ።



ሀ እና ሐ ከመረጡ ትክክል ነዎት!

ግለሰቡን ወደ ጆሮ እና የመስማት ችሎታ ባለሙያ ሪፈር ያድርጉ እና ከህክምናው በኋላ ለጆሮ ጤና ልየታ እንዲመለስ ይጠይቁ።

የቅጹ የጆሮ ጤና ምርመራ ክፍል። 'ሁለቱም ጆሮዎች ጤናማ ይመስላሉ' በሚለው ክፍል ላይ 'አይ' የሚል ምልክት ተደርጎበታል።

ጥያቄ

1. የግራ ጆሮ ውስጠኛ ክፍል ምስል ይመልከቱ። ምን ይታይዎታል?

አንዱን ይምረጡ።

የግለሰቡ የግራ ጆሮ ቦይ ግልጽ ነው። የጆሮው ታምቡር ግልጽ እና ነጭ/ነጣ ያለ ግራጫ ቀለም ነው።





ሠ ከመረጡ ትክክል ነዎት!

የግራ ጆሮ ጤናማ ነው - ምንም የጆሮ ችግር የለም። 

2. የቀኝ ጆሮውን የውስጠኛ ክፍል ምስል ይመልከቱ። ምን ይታይዎታል?

አንዱን ይምረጡ።

የአንድ ሰው የቀኝ ጆሮ ቦይ በቢጫ እና ቡናማ ጆሮ ሰም ተዘግቷል።





ለ  ከመረጡ ትክክል ነዎት!

የቀኝ ጆሮ ቱቦ በጆሮ ሰም ተዘግቷል። 

3. ለዚህ ሰው ምን እርምጃ ትወስዳለህ?

አንዱን ይምረጡ።





ለ  ከመረጡ ትክክል ነዎት!

የግለሰቡን የቀኝ ጆሮ በጆሮ ሰም ተደፍኖል። የጆሮውን ሰም ለማስወገድ ጆሮ አጠባ ማድረግ ምንም ጉዳት የማያደርስ መሆኑን ያረጋግጡ። ከተወገደ በኋላ ጆሮን ይፈትሹ። 

የቅጹ የጆሮ ጤና ምርመራ ክፍል። የቀኝ ጆሮ 'በጆሮ ሰም የተደፈነ ጆሮ' የሚል ምልክት ተደርጎበታል። የግራ ጆሮ ጤናማ ነው።

ተግባር

መሳሪያዎችን መሰብሰብ፦

  • ኦቶስኮፕ እና የተለያየ መጠን ያላቸው ስፔኩለም
  • ስፔኩለሙን ለማጽዳት ፀረ-ተዋሲያን እና ቲሹ
  • ሁለት ወንበሮች።

ተራ በተራ ይለማመዱ፦

  1. ምን ሊያደርጉ እንደሆነ ያስረዱ
  2. በእያንዳንዱ ጎን የግለሰቡን የጆሮውን ውጫዊ ክፍል ይፈትሹ
  3. በእያንዳንዱ ጎን ያለውን የግለሰቡን የጆሮ ውስጠኛ ክፍል ከመፈተሾ በፊት ህመምን እንዳለ ለማረጋገጥ ትራገስን በቀስታ ይጫኑ።

ግብረ መልስ

  • የግለሰቡን የጆሮ ውስጠኛ ክፍል ማየት ችለዋል?
  • የጆሮ ጤና ችግር ምልክቶች አግኝተዋል?

ትምህርት ሶስትን ጨርሰሃል!