ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
መስማት

የማጣራት ጥያቄዎች

ትምህርት፡- 3 የ 5
ርዕስ፡- 2 የ 5
0% ተጠናቋል

አንዳንድ ጥያቄዎችን እንደምትጠይቅ ለግለሰቡ ግለጽለት። የእነሱ መልሶች ከእነሱ ጋር አብረህ በመስራት እቅድ እንድታወጣ ይረዳሃል። 

ተገቢ ሲሆን የቤተሰብ አባላትን ወይም ተንከባካቢዎችን ያሳትፉ።

የመስማት ረዳት ምርቶች 

መመሪያ

ይጠይቁ፦ በአሁኑ ጊዜ በመስማት አገልግሎት በኩል የቀረበ የመስማት ረዳት ምርት ይጠቀማሉ?

ግለሰቡ ቀደም ሲል የመስማት ረዳት ምርትን ከተጠቀመ የጆሮ ጤና ማጣሪያ ምርመራን ያጠናቅቁ። ከዚያም፡-

  • ምን ዓይነት የመስማት ረዳት ምርት እየተጠቀሙ እንደሆነ ያስተውሉ
  • በሚጠቀሙት ምርት ላይ ችግሮች እያጋጠማቸው ከሆነ ይፈትሹ።

ግለሰቡ አሁን ባለው የመስሚያ ረዳት ምርታቸው ላይ ችግር ካጋጠማቸው እና  ፈቃደኛ ከሆኑ፤ ግለሰቡ ምርቱን ወደ ተቀበለበት አገልግሎት ሪፈር ያድርጉ።

ጥያቄ

ካሌይሻን ያግኙ

ካሌይሻ 79 ዓመቷ ነው እና ቤተሰቧን እየጎበኘች ነው። የመስሚያ አጋዥ መሳሪያዎችዋን ስትጠቀም ችግር እያጋጠማት ነው።

ካሌይሻ የመስሚያ አጋዥ መሳሪያዎችን መልበስ አቁማለች እና  የመስማት ችግር እያጋጠማት ነው። ከቤተሰብ ውይይቶች ጋር መቀላቀል ይከብዳታል።

ካሌይሻ ወደ ጤና ጣቢያ ሄደች። የጤና ባለሙያው የጆሮ ጤና ማጣሪያ ምርመራ ያካሄዳል። ጆሮዋ ጤናማ ነው።

ቀጥሎ ምን እርምጃ ትመክራለህ?

አንዱን ይምረጡ።




ለ  ከመረጡ ትክክል ነዎት!

የTAP ጆሮ ጤና ማጣሪያ ምርመራ ቅጽ የማጣሪያ ጥያቄዎች ክፍል። ለአሁኑ የመስማት ረዳት ምርት ጥያቄ ሳጥኑ 'አዎ' የሚል ምልክት ተደርጎበታል።

ካሌይሻን ከተቻለ የመስሚያ አጋዥ መሳሪያዎችን ወደ ሰጠው አገልግሎት ሪፈር ማድረግ አስፈላጊ ነው። አገልግሎቱ የመስሚያ አጋዥ መሳሪያዎችን ማስተካከል እና አስፈላጊ ከሆነ መለዋወጫዎችን መስጠት ይችላል።

የሚወራ ቋንቋ

መመሪያ

ጠይቅ፦ ለመግባባት ንግግርን መጠቀም ተቸግረሃል?

አንዳንድ አዋቂዎች እና ልጆች ንግግርን ለመጠቀም ይቸገራሉ።

ንግግርን እንደ ተለመደው የመግባቢያ መንገድ የማይጠቀም ሰው የበለጠ ውስብስብ ፍላጎቶች አሉት። የጆሮ እና የመስማት ችሎታ ባለሙያ ሪፈር ያድርጉ።

መመሪያ

በTAP የተግባቦት ረዳት ምርቶች ሞጁል ውስጥ የመግባባት ችግር ላጋጠማቸው ሰዎች የበለጠ ይወቁ።

በመስማት ላይ ድንገተኛ ለውጦች

መመሪያ

ይጠይቁ፦ ባለፉት 3 ወራት ውስጥ የመስማት ችሎታ ላይ ድንገተኛ ለውጦች አጋጥመውዎታል?

አንድ ሰው በጊዜ ሂደት ቀስ በቀስ የመስማት ችግር ያጋጥመዋል።

ማስጠንቀቂያ

አንድ ሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ (ባለፉት ሶስት ወራት) የመስማት ችሎታ ላይ ድንገተኛ ለውጦች ካጋጠመው ከባድ የጤና ችግርን ሊያመለክት ይችላል። ወዲያውኑ ወደ ጆሮ እና የመስማት ችሎት ባለሙያ ሪፈር ያድርጉ ።

ከጆሮው ተደጋጋሚ ፈሳሽ

መመሪያ

ይጠይቁ፦ ፈሳሽ (ፈሳሽ) ብዙ ጊዜ ከጆሮዎ/ች ይወጣል?

አንድ ሰው ከጆሮው የሚወጣ ቀለም ያለው ፈሳሽ አለ።

አንድ ሰው ብዙ ጊዜ ከጆሮው የሚወጣ ፈሳሽ ካጋጠመው፤ ይህ ተደጋጋሚ የጆሮ ኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል። 

ፈሳሹ ያልተለመደ ቀለም ሊኖረው ይችላል። በተጨማሪም ሽታ ሊኖረው ይችላል።

ተደጋጋሚ የጆሮ ኢንፌክሽን የግለሰቡን ጆሮ እና የመስማት ችሎታ ይጎዳል። በእነሱ ፍቃድ ለግምገማ የጆሮ እና የመስማት ባለሙያን ሪፈር ያድርጉ።

ጋሬትን አስታውስ?

ጋሬት የ9 አመት ልጅ ሲሆን በአሳ ማጥመጃ መንደር ውስጥ ይኖራል። ከጓደኞቹ ጋር በውሃ ውስጥ መዝለቅ ይወዳል። ጋሬት ብዙ ጊዜ ከጆሮው የሚፈሰ ፈሳሽ እና  የሚያሰቃይ ህመም በጆሮ ላይ ይሰማዋል።

ጥያቄ

በተደጋጋሚ የጆሮ ኢንፌክሽን ያጋጠመው ሰው ወደ ጆሮ እና የመስማት ችሎታ ባለሙያ ረፊር መደረግ አለበት?

አንዱን ይምረጡ።


አዎ ልክ ነው!

በተደጋጋሚ የጆሮ ኢንፌክሽን እና የጆሮ ፈሳሽ ያጋጠመው ሰው ወደ ጆሮ እና የመስማት ችሎታ ባለሙያ ሪፈር መደረግ አለበት።

ውይይት

የትኞቹን የጆሮ እና የመስማት ባለሙያዎች ሪፈር ለማድረግ በአካባቢው ይገኛሉ?

አንድን ሰው ወደ እነዚህ አገልግሎቶች እንዴት ሪፈር እንደሚደረግ ያውቃሉ?

0%
የማጣራት ጥያቄዎች
ትምህርት፡- 3 የ 5
ርዕስ፡- 2 የ 5