ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
መስማት

የTAP ጆሮ ጤና ልየታ መግለጫ

ትምህርት፡- 3 የ 5
ርዕስ፡- 1 የ 5
0% ተጠናቀቀ

መመሪያ

እስካሁን ካላደረጉት፣ የ የTAP የጆሮ ጤና ልየታ ምርመራ ቅጽ በአዲስ ታብ ወይም ዊንዶው ያውርዱ እና ፕሪንት ያድርጉ።

አገልግሎትዎ የተለየ ቅጽ ከተጠቀመ፤ ይህንን ከሱፐርቫይዘርዎ ጋር ይወያዩ።

የTAP ጆሮ ጤና ልየታ አንድ ልጅ ወይም አዋቂ የጆሮ ችግር እና/ወይም የመስማት ችግር እንዳለበት ለማወቅ የሚደረግ ቀላል ሂደት ነው።

የTAP ጆሮ ጤና ልየታ አንድ ሰው እነዚህን ሊፈልግ ይችል እንደሆነ ለመለየት ይረዳል፡-

  • በደረቅ ጨረቅ ያጽዱ ወይም ጆሮውን ይጠቡ
  • በTAP ውስጥ ከተካተቱት የመስማት አጋዥ ምርቶች ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ ለማረጋገጥ የመስማት ችሎታ ምርመራ ማካሄድ 
  • ለምርመራ ወደ ጆሮ እና የመስማት ባለሙያ ሪፈር ማድረግ 
  • ለሌሎች አጋዥ ምርቶች ሪፈራል።

 የTAP ጆሮ ጤና ልየታ ቅጽ ይጠቀሙ፦

  • በጆሮ ጤና ልየታ ደረጃዎች ይመራዎታል
  • የልየታውን ውጤቶችን ይመዝግቡ
  • ተግባራትን ያቅዱ። 

መመሪያ

ይህን አዶ ባዩ ቁጥር ሰውየው ሪፈራል ሊፈልግ ይችላል ማለት ነው።

ቦታ እና መሳሪያዎች

የጆሮ ጤና ልየታ ለማካሄድ ቦታ ያስፈልግዎታል ይህም፦

  • ለተገልጋዩ እና ለእርስዎ ወንበር ያለው
  • እያንዳንዱን ሰው ከመመርመርዎ በፊት እና በኋላ እጅዎን የሚታጠቡበት ቦታ ያለው።

ያስፈልግዎታል፡-

  • ኦቶኮስኮፕ እና ስፔኩለም(ዎች)
  • በደረቅ ጨረቅ ለማጠብ ቲሹዎች
  • የጆሮ ማጠቢያ መሳሪያ
  • ለእያንዳንዱ ሰው አንድ የTAP ጆሮ ጤና መለያ ቅጽ።

ለግለሰቡ ያስረዱ፡-

የጆሮ ችግር ምልክቶች እንዳሉ ያረጋግጣሉ።

በልየታው ወቅት የሚከተሉትን ይመለከታሉ፦

  • የጆሮአቸው ጤና
  • የጆሮ እና የመስማት ችሎታ ባለሙያ ማየት የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ወይም
  • በመስማት ምርመራ መረዳት የሚችሉ ከሆነ።

መመሪያ

ጠይቅ፦

  • ማንኛውም ጥያቄ አለህ?
  • የጆሮ ልየታ እንዲደረግ ፍቃድ ሰጥተሃል?

ልጆችን የሚመረምሩ ከሆነ ከልጁ እና ከወላጆቻቸው ወይም ከአሳዳጊው ፈቃድ ይጠይቁ።

ስለ ተገልጋዩ መረጃ

የTAP የጆሮ ጤና ልየታ የመጀመሪያ ክፍል የመገኛ መረጃ መሰብሰብ ሲሆን ይህም ስለ ግለሰቡ ስም፣ ጾታ፣ ዕድሜ፣ ስልክ እና አድራሻ ያካትታል።

መመሪያ

ስለ ግለሰቡ አጠቃላይ መረጃ በመሰብሰብ ይጀምሩ።

ዕድሜ

እድሜአቸው ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህጻናት የበለጠ ውስብስብ የጤና ፍላጎቶች አሏቸው። ከቤተሰባቸው አባል ፈቃድ በመጠየቅ ወደ ጆሮ እና የመስማት ችሎታ ባለሙያ ሪፈር ያድርጉ።

መመሪያ

የጆሮ ጤና ልየታ ከማድረግዎ በፊት እንዴት እንደሚደረግ ማወቅ ጠቃሚ ነው፡-

  • ኦቶስኮፕ ይጠቀሙ
  • በደረቅ ጨርቅ ያጽዱ እና ጆሮውን ይጠቡ።

ስለእነዚህ ክህሎቶች በርዕስ ሶስት እና አራት ውስጥ ይማራሉ።