ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
መግቢያ

በምርት አቅርቦት ውስጥ የተለያዩ ሚናዎች

ትምህርት፡- 2 የ 5
ርዕስ፡- 1 የ 1
0% ተጠናቀቀ

በገበያው አካባቢ አውቶቡስ ቆሟል። አንድ ሰው ለሁለት ሴቶች በሩን ከፈተ። ከሴቶቹ አንዷ ምርኩዝ ትጠቀማለች። በበሩ ፊት ለፊት አንድ ትንሽ ደረጃ አለ።

 ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን የአጋዥ ምርቶች እንዲያገኙ በመደገፍ ረገድ ሚና የሚጫወቱ ብዙ ሰዎች አሉ። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • አጋዥ ምርት የሚያስፈልገው ሰው እና ቤተሰባቸው
  • ከአጋዥ ምርቶች ሊጠቅም የሚችልን ሰው የሚለዩ እና ወደ አጋዥ የምርት አገልግሎት ሪፈር የሚያደርጉ ሰዎች
  • ተገቢውን አጋዥ ምርቶችን ለማቅረብ ከግለሰቡ ጋር አብረው የሚሰሩ የሰለጠኑ ሰራተኞች
  • አጋዥ ምርቶችን የሚጠቀሙ ሰዎችን በመደገፍ የማህበረሰብ አባላት በሙሉ ሚና ያላቸው ።
  • መሪዎች እና ውሳኔ ሰጪዎች ለምሳሌ አጋዥ ምርቶችን በማህበረሰባዊ ስርአት በኩል እንዲቀርቡ የሚያደርጉ ወይም ማህበረሰብ የሚያዘወትርባቸው ቦታዎች እና መጓጓዣዎች አጋዥ ምርቶችን ለሚጠቀሙ ሰዎች ተደራሽ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ።

የድጋፍ ሰጪ ሠራተኛ ከሚካኤል እና ከወላጆቹ ጋር የምርመራ ቃለ መጠይቅ ያደርጋል። ሁሉም በቡድን ተቀምጠዋል።

ሚካኤል እና ጓደኛው በአሸዋማ መንገድ ላይ አብረው ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ። ሚካኤል ከፊት ለፊት ነው፣ እና ከፊት ለፊቱ ያለውን መንገድ ለመለየት ጫፉ ላይ ክብ ኳስ ያለው ነጭ ዘንግ እየተጠቀመ ነው።

ሚካኤልን አግኝ።

ሚካኤል አይነ ስውር ሆኖ ነው የተወለደው። ትምህርት ሲጀምር ወላጆቹ የአካል ጉዳተኞችን ስለሚረዳ የማህበረሰብ ድርጅት ሰሙ። ድርጅቱን አነጋግረው እርዳታ ጠየቁ።

አንድ የድጋፍ ሰጪ ሠራተኛ ሚካኤልን እና ቤተሰቡን ለመጠየቅ ወደ ቤታቸው መጣ። በዚህ ጉብኝት ወቅት ሚካኤል እና ቤተሰቡ ብቻውን መንቀሳቀስ እንደሚፈልግ አስረድተዋል። የድጋፍ ሰጪ ሰራተኛው ሚካኤል ነጭ ዘንግ ቢጠቀም ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል። ሚካኤል በድርጅቱ ማእከል እንዲመረምር ቀጠሮ ተይዞለታል።

ሚካኤል ወደ ትምህርት ቤት ለመድረስ እና ለመመለስ እንዲሁም በክፍሉ እና በመጫወቻ ስፍራው ውስጥ በሰላም ለመዘዋወር የሚጠቀምበት ነጭ ዘንግ ተሰጠው።

የድጋፍ ሰጪው ሰራተኛ ነጭ ዘንግን ስለመጠቀም እና ሚካኤል በክፍል እና በመጫወቻ ስፍራው ውስጥ በደህና እንዲንቀሳቀስ እንዴት እንደሚረዱት በክፍሉ ውስጥ ያሉትን ልጆች አነጋግሯል። አሁን ሁሉም ሰው በትምህርት ቤቱ ኮሪደሮች እና መንገዶች ላይ መሰናክሎችን ላለመተው ሁልጊዜ ይሞክራሉ!

ጥያቄ

  • ሚካኤል ነጭ ዘንጉንን እንዲያገኝ እና እንዲጠቀም የረዱት ሰዎች እነማን ነበሩ?
  • እያንዳንዱ ሰው ምን ሚና ተጫውቷል?
  • ድርጅቱን ያነጋገሩ እና በጉብኝቱ ወቅት ሚካኤልን የሚደግፉ የሚካኤል ወላጆች
  • ሚካኤልን የጎበኘው የማህበረሰቡ ድጋፍ ሰጭ እና ግምገማ እንዲደረግለት አመቻችቶል
  • ሚካኤል በራሱ መንቀሳቀስ እንደሚፈልግ ገልጿል።
  • የሚካኤል አስተማሪዎች እና የክፍል ጓደኞቹ በትምህርት ቤት ነጩን ዘንግ ሲጠቀም እየደገፉት እና በኮሪደሮች እና በመንገዶቹ ላይ ያሉ እንቅፋቶችን ለመቀነስ እየሰሩ ነው።

ማቲያስ እና ሚስቱ በጤና ክሊኒክ ተቀምጠው ነርስ ሲያወሩ።

ማቲያስን አስታውስ?

ማቲያስ የስኳር በሽታ አለበት, እና በአካባቢው የጤና ክሊኒክ ውስጥ ከነርስ ጋር መደበኛ ቀጠሮዎች አሉት.

በአንድ ቀጠሮ ወቅት ነርሷ ማቲያስ በእግር ሲራመድ ቀጥ ብሎ እንዳልሆነ አስተውላለች። ማቲያስ ቶሎ ስለሚደክመው መራመድ እንደሚከብደው ገለጸ።

ነርሷ ማቲያስን ወደ ክሊኒኩ የማህበረሰብ ሰራተኛ ሪፈር አድርጋለች። የማህበረሰቡ ሰራተኛው የእንቅስቃሴ መለያ ምርመራ ካደረገ በኃላ ማቲያስ የመራመጃ አጋዥ ቢጠቀም ተጠቃሚ እንደሚሆን ተገንዝቧል እና እግሩ እንዳይጎዳ ለመከላከል የሚለብሰው ተስማሚ ጫማ እንዲጠቀም መክሮታል። ከመራመጃ አጋዥ ምርመራ በኋላ የማህበረሰብ ሰራተኛው ለማቲያስ ሮሌተር ሰጠው።

ማቲያስ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የመራመጃ አጋዥ መሣሪያን የተጠቀመ ሁለተኛው ሰው ነበር። የቤተክርስቲያኑ ኮሚቴ ለሁሉም ሰው ተደራሽ ለማድረግ ራምፕ ለመስራት ወስኗል።

በክሊኒኩ ውስጥ በተደረገ የክትትል ቀጠሮ ወቅት፤ የማህበረሰቡ ሰራተኛ ማቲያስ የራሱን እንክብካቤ እንዴት እንደሚቆጣጠር (እንደ መጸዳጃ ቤት መሄድ እና/ወይም እራሱን ማጠብ) ጠይቆት ነበር። ማቲያስ የሽንት አለመቆጣጠር ችግር ስላጋጠመው ወደ ውጭ መውጣት እንዳቆመ ተናግሯል። በነርሷ ከተመረመረ በኋላ፤ ማቲያስ ወደ ማህበረሰቡ በሚወጣበት ጊዜ የሚጠቀማቸው የሚመጡ ጨርቆችን(absorbent cloths) ቀርቦለታል። አሁን ማቲያስ ወደ ውጭ ለመውጣት በራስ መተማመን አለው።

ጥያቄ

  • ማቲያስ አጋዥ ምርቶችን እንዲያገኝ እና እንዲጠቀም በመርዳት ላይ የተሳተፉት እነማን ነበሩ?
  • እያንዳንዱ ሰው ምን ሚና ተጫውቷል?
  • ማቲያስ ከረዳት ምርቶች እንደሚጠቀም ያስተዋለችው ነርስ። ለእንቅስቃሴ ማጣሪያ ምርመራ ወደ አንድ የማህበረሰብ ሰራተኛ ሪፈር አድርጋዋለች እና በኋላም ሽንት ያለመቆጣጠር ችግሩን በመገምገም ረድታለች።
  • መራመጃ አጋዥ ለማቅረብ የገመገመው የማህበረሰብ ሰራተኛ፤ ስለራስ እንክብካቤ ፍላጎቱ ማቲያስን ጠየቀው።
  • ማቲያስ መራመድ እየከበደው እንደሆነ እና ሽንቱን መቆጣጠር ባለመቻሉ ምክንያት ወደ ውጭ መውጣት እንደማይፈልግ አስረድቷል።
  • በቤተክርስቲያን ውስጥ የመራመጃ አጋዡን በተሳካ ሁኔታ መጠቀም እንደሚችል ያረጋገጠለት የቤተክርስቲያኑ ማህበረሰብ።

ከዚህ ቀደም እንዳየነው ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን የአጋዥ ምርቶች እንዲያገኙ በመደገፍ ሚና የሚጫወቱ ብዙ ሰዎች አሉ።

ትምህርት ሁለትን ጨርሰሃል!