ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
መግቢያ

ደረጃ ሁለት - ተስማሚነት

ትምህርት፡- 3 የ 5
ርዕስ፡- 3 የ 5
0% ተጠናቋል

ደረጃ ቁጥር 2 ከ 4ን የሚወክል ስዕላዊ ገለጻ።

ሁለተኛው ደረጃ ረዳት ምርት ተስማሚ እንደሆነ ያካትታል።

አግዳሚ ወንበር ላይ ቆሞ ምርኩዝ የያዘ አገልግሎት አቅራቢ።

አንዴ የረዳት ምርቱ ከተመረጠ በኃላ አገልግሎት አቅራቢው ረዳት ምርቱ እንደዚህ መሆኑን ያረጋግጣል፡-

  • በትክክል ተሰብስቧል
  • በትክክለኛው መጠን ተስተካክሏል
  • ለአንድ ሰው ለመጠቀም ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ

በዚህ ደረጃ ከግለሰቡ ቀጥተኛ ግብረመልስ ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው።

እንደ ረዳት ምርቱ፣ ተስማሚነቱን ማረጋገጥ ምርቱ ከግለሰቡ ፍላጎት ጋር የሚስማማ መሆኑን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ማስተካከያዎችን እና/ወይም ማሻሻያዎችን ማድረግን ሊያካትት ይችላል።

አንድ አገልግሎት ሰጪ ሚካኤል ነጭ ዱላ እንዲሞክር እየረዳው ነው። ዱላውን በሚጠቀመው ሚካኤል ላይ አንድ እጁን፣ ሌላኛው ደግሞ እሱን ለመምራት እንዲረዳው በሚካኤል ትከሻ ላይ ነው።

በዚህ ምሳሌ ላይ አንድ አገልግሎት አቅራቢ ከሚካኤል ጋር በመስራት ነጭ ዱላው ትክክለኛ ርዝመት እንዳለው ያረጋግጣል። ዱላው ሚካኤል ሲራመድ ከፊት ለፊቱ ያለውን መሬት ለመቃኘት በቂ ርዝመት ሊኖረው ይገባል።

ትክክል ተስማሚ መሆኑ በጣም አስፈላጊ ነው። አንድ ምርት በደንብ የማይስማማ ከሆነ፤ ጥሩ ላይሰራ ይችላል፤ የማይመች እና/ወይም ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

ማቲያስ ሮላተሩን ተጠቅሞ እንዲራመድ የሚያግዘው አገልግሎት ሰጪ። አገልግሎት ሰጪው  ከማቲያስ ጎን እና ጀርባ ቆሞ ሁለቱም እጆቹ በወገቡ ላይ ናቸው። ማቲያስ ሮለተሩን በሁለት እጆቹ ይዞል።

ማቲያስን አስታውስ?

ማቲያስ በቤቱ እና በአትክልቱ ስፍራ ለመዞር ሮለተር ይጠቀማል። ሮለተሩን ሲቀበል አገልግሎት ሰጪው ለማቲያስ በትክክለኛው ከፍታ ላይ መሆኑን አረጋግጧል። ማቲያስ ከሮላተሩ ጋር መራመድን እንዲለማመድ ረዱት እና ምቾት እንደሚሰማው ጠየቁት። ፍሬኑን በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን አረጋግጠዋል።

0%
ደረጃ ሁለት - ተስማሚነት
ትምህርት፡- 3 የ 5
ርዕስ፡- 3 የ 5