ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
ዕይታ

ቁልፍ ቃላት

ትምህርት፡- 1 የ 5
ርዕስ፡- 1 የ 2
0% ተጠናቀቀ

መመሪያ

በዚህ ሞጁል ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ አንዳንድ ቁልፍ ቃላት ከዚህ በታች ተብራርተዋል። ሞጁሉን ሲያነቡ ለመጠቀም እነዚህን ፕሪንት ማድረግ ይችላሉ፡-

አስቲግማቲዝም - አስቲግማቲዝም ያለባቸው ሰዎች በሩቅ እና በቅርብ ለማየት እና ይቸገራሉ።

የፈረስ ጭንቅላት እና አንገት ከፊት ለፊቱ ሌላ ፈረስ የሚጋልብ ሰው አለ። ምስሉ በሙሉ ደብዛዛ ነው።

የስኳር በሽታ - ስኳር በደም ውስጥ ከፍተኛ ሲሆነ ። ይህ የሰውነት ክፍሎችን (በተለይ እግሮችን) የመሰማት መቸገር እና የእግር ቁስሎች፣ ቀስ በቀስ የእይታ ማጣት፣ የኩላሊት መጎዳት፣ የሽንት መቆራረጥ እና ነገሮችን ለማስታወስ መቸገርን ጨምሮ ለብዙ የጤና ችግሮች ያስከትላል።

ሃይፐሮፒያ - ሃይፐሮፒያ ያለባቸው ሰዎች 'ሎንግ ሳይትድ'  ናቸው። በሩቅ ያሉትን ነገሮች በግልፅ ማየት ይችላሉ፤ ነገር ግን በቅርብ ነገሮች ላይ ማተኮር ይከብዳቸዋል።

የፈረስ ጭንቅላት እና አንገቱ ደብዛዛ፣ ከፊት ለፊታቸው ሌላ ፈረስ የሚጋልብ ሰው አለ። የምስሉ የፊት ገጽታ ደብዛዛ ነው።

የመማር እክል - የመማር እክል ያለበት ሰው የመግባባት እና ራስን መንከባከብን ጨምሮ አዳዲስ ክህሎቶችን በመማር ላይ አንዳንድ ገደቦች ሊኖሩት ይችላል።

ማዮፒያ - ማዮፒያ ያለባቸው ሰዎች 'ሾርት ሳይትድ' ናቸው። ቅርብ የሆኑ ነገሮችን በግልፅ ማየት ይችላሉ፣ነገር ግን ብዙ ራቅ ያሉ ነገሮች ደብዛዛ ናቸው።

የፈረስ አንገትና ጭንቅላት በግልጽ ይታያል፣ ከፊት ለፊቱ ሌላ ሰው በፈረስ ላይ ተቀምጧል። የምስሉ ዳራ ግልፅ አይደለም (ደብዛዛ)።

ኦክሌደር - ዓይንን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ነገር።

እጀታ እና ክብ ጫፍ ያለው የፕላስቲክ ቁስ።

ሰራተኛ - በአገልግሎት ወይም ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ናቸው። በልዩ ከጤና ጋር በተገናኘ የትምህርት ዘርፍ ሥልጠና የወሰዱ ሰዎችን ያጠቃልላል፤ እነሱም በአይን ህክምና ሙያ ያልተመረቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

ሪፍራክቲቭ ኢረር - ለዕይታ ችግሮች የተለመደ ምክንያት ሲሆን ብዙውን ጊዜ ከትክክለኛ መነጽር ወይም በአይን ሌንሶች ይስተካከላል። ወደ ተለያዩ የእይታ ችግሮች የሚያመሩ የተለያዩ ሪፍራክቲቭ ኢረሮች አሉ። አንዳንድ ምሳሌዎች አስትግማቲዝም፣ ሃይፐሮፒያ እና ማዮፒያ ያካትታሉ።

መመሪያ

የማታውቋቸው ሌሎች ቃላት ካገኙ የስራ ባልደረባዎን ወይም አሰልጣኝዎን ይጠይቁ።