ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
መግቢያ

ሰዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ረዳት ምርቶችን እንዲጠቀሙ መደገፍ

ትምህርት፡- 4 የ 5
ርዕስ፡- 2 የ 2
0% ተጠናቋል

ለብዙ ሰዎች ረዳት ምርቶችን ማግኘት በሚፈልጉት ወይም በሚያስፈልጋቸው ተግባራት ላይ መሳተፍ የመቻል ያህል አስፈላጊ ነው።

በትክክለኛው የረዳት ምርትም ቢሆን እንኳን ሰዎች ተሳትፏቸውን የሚገድቡ መሰናክሎች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ።

እነዚህ መሰናክሎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

  • ተደራሽ ያልሆነ አካባቢ
  • ማህበራዊ መገለል እና አድልዎ
  • የተደራሽ መረጃ እጥረት
  • የድጋፍ አገልግሎቶች ወይም ፖሊሲዎች እጥረት።

ረዳት ምርቶችን የሚጠቀሙ ሰዎች በሚፈልጉት ወይም በሚያስፈልጋቸው ተግባራት ከሌሎች ጋር በእኩልነት እንዲሳተፉ ለማድረግ ሁሉም ሰው ሚና አለው።

ሌይ ሐምራዊ ቲሸርት ለብሳ ቆማለች። አንድ ክንድ ከጎኗ ሲኖራት ሌላኛው ደግሞ ወደ ሰውነቷ ታጠፎ።

ከሌይ ጋር ተገናኙ።

ሌይ ስትሮክ አጋጠሞታል እና ከልጇ ጋር እቤት ትኖራለች። የሌይ አካል የቀኝ ጎን ደካማ ነው እና አንዳንድ ጊዜ ንግግሯ ግልጽ አይደለም። እሷን ለመዘዋወር እንዲረዳት ምርኩዝ ትጠቀማለጭ

ከስትሮክ በፊት ሌይ በማህበረሰቡ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ነበረች እና ብዙ ጊዜ አትክልቶችን በአካባቢው ገበያ ትሸጥ ነበር። ሆኖም ከስትሮክ በኋላ ወደ ገበያ ለመሄድ ወደ አውቶቡሱ ለመግባት ተቸግራለች። በገበያው ላይ የነበሩ አንዳንድ ሴቶች እሷን በንግግራቸው እና በተግባራቸው ማካተት እንዳቆሙ አስተውላለች።

በገበያው አካባቢ አውቶቡስ ቆሟል። አንድ ሰው ለሁለት ሴቶች በሩን ከፈተላቸው አንደኛዋ ምርኩዝ ትጠቀማለች።

ሌይ ብቸኝነት ተሰማት እና ብዙ ጊዜ ወደ ገበያ አትሄድም። ሆኖም አንድ ቀን የአውቶቡስ ሹፌር የሰራውን ትንሽ ተንቀሳቃሽ ደረጃ ለሌይ አሳያት፤ ይህም ወደ አውቶቡሱ ለመውጣትና ለመውረድ በጣም ቀላል አድርጎታል።

ሌይ እና ጓደኛዋ ከገበያ ድንኳናቸው ጀርባ አትክልት እየሸጡ ጎን ለጎን ቆመው ነበር።

በገበያ ላይ የምትገኝ የሌይ ጓደኛም ከሌሎች ሴቶች ጋር እንድትነጋገር ረዳቻት እና ሌይ አሁንም መረዳት እና በውይይት መሳተፍ እንደምትችል ነገር ግን በግልጽ ለመናገር ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልጋት አስረዳች። ሌሎቹ ሴቶች ተረድተው እሷን እንደገና በተግባሮቻቸው እና ንግግራቸው ውስጥ አካትቷት እናም ምላሽ ለመስጠት የምትፈልገውን ያህል ጊዜ ይሰጥዎታል።

ሌይ እንደገና አትክልቶቿን በገበያ ትሸጣለች እና ከሌሎች ሴቶች ጋር መነጋገር ትወዳለች።

ጥያቄ

1. ሌይ ከተሳትፎ መሰናክሎች ምን አጋጥሟት?

1. ሌይ ያጋጠማት፡-

  • የአካል መሰናክሎች (ወደ አውቶቡስ ለመግባት ከበዳት)
  • የአመለካከት እንቅፋቶች (በገበያ ላይ ያሉ ሴቶች ሌይን ከንግግራቸው እና ከተግባራቸው አገለሉ)።

2. እንዴት ነው ማሸነፍ የቻለችው? የተለያዩ ሰዎች ምን ሚና ተጫውተዋል?

2. በማኅበረሰቧ ውስጥ ባሉ ሰዎች ድጋፍ እንቅፋቶችን አሸንፋለች፡-

  • የአውቶቡስ ሹፌር ሌይ ከአውቶቡሱ እንድትወጣ እና እንድትወርድ ተንቀሳቃሽ ደረጃዎች(portable step) በማድረግ የአካል መሰናክሎችን እንድታሸንፍ ረድቷታል።
  • ሌይ አሁንም በንግግራቸው እና በተግባራቸው መሳተፍ እንደምትችል እንዲረዱ የሌይ ጓደኛ ከሌሎች ሴቶች ጋር እንድትነጋገር ደገፈቻት።

ትምህርት አራት ጨርሰሃል!

ማንኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት ካለዎት በውይይት መድረክ ላይ ይለጥፉ።

0%
ሰዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ረዳት ምርቶችን እንዲጠቀሙ መደገፍ
ትምህርት፡- 4 የ 5
ርዕስ፡- 2 የ 2