ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
መግቢያ

በረዳት ምርት አቅርቦት ውስጥ የተለያዩ ሚናዎች

ትምህርት፡- 2 የ 5
ርዕስ፡- 1 የ 1
0% ተጠናቋል

በገበያው አካባቢ አውቶቡስ ቆሟል። አንድ ሰው ለሁለት ሴቶች በሩን ከፈተ። ከሴቶቹ አንዷ ምርኩዝ ትጠቀማለች። በበሩ ፊት ለፊት አንድ ትንሽ ደረጃ አለ።

 ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን የእርዳታ ምርቶች እንዲያገኙ በመደገፍ ረገድ ሚና የሚጫወቱ ብዙ ሰዎች አሉ። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ረዳት ምርት የሚያስፈልገው ሰው እና ቤተሰባቸው
  • ከረዳት ምርቶች ሊጠቅም የሚችልን ሰው የሚለዩ እና ወደ ረዳት የምርት አገልግሎት ሪፈር የሚያደርጉ ሰዎች
  • ተገቢውን ረዳት ምርቶችን ለማቅረብ ከግለሰቡ ጋር አብረው የሚሰሩ የሰለጠኑ ሰራተኞች
  • ረዳት ምርቶችን የሚጠቀሙ ሰዎችን በመደገፍ የማህበረሰብ አባላት በሙሉ ሚና ያላቸው ።
  • መሪዎች እና ውሳኔ ሰጪዎች ለምሳሌ ረዳት ምርቶችን በህዝባዊ ሲስተም በኩል እንዲቀርቡ የሚያደርጉ ወይም የህዝብ ቦታዎች እና መጓጓዣዎች ረዳት ምርቶችን ለሚጠቀሙ ሰዎች ተደራሽ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ።

የድጋፍ ሰጪ ሠራተኛ ከሚካኤል እና ከወላጆቹ ጋር የግምገማ ቃለ መጠይቅ ያደርጋል። ሁሉም በቡድን ተቀምጠዋል።

ሚካኤል እና ጓደኛው በአሸዋማ መንገድ ላይ አብረው ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ። ሚካኤል ከፊት ለፊት ነው፣ እና ከፊት ለፊቱ ያለውን መንገድ ለመለየት ጫፉ ላይ ክብ ኳስ ያለው ነጭ ዱላ እየተጠቀመ ነው።

ሚካኤልን አግኝ።

ሚካኤል ዕውር ሆኖ ነው የተወለደው። ትምህርት ሲጀምር ወላጆቹ የአካል ጉዳተኞችን ስለሚረዳ የማህበረሰብ ድርጅት ሰሙ። ድርጅቱን አነጋግረው እርዳታ ጠየቁ።

አንድ የድጋፍ ሰጪ ሠራተኛ ሚካኤልን እና ቤተሰቡን ለመጠየቅ ወደ ቤታቸው መጣ። በዚህ ጉብኝት ወቅት ሚካኤል እና ቤተሰቡ ብቻውን መንቀሳቀስ እንደሚፈልግ አስረድተዋል። የድጋፍ ሰጪ ሰራተኛው ሚካኤል ነጭ ድላ ቢጠቀም ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል። ሚካኤል በድርጅቱ ማእከል እንዲገመገም ቀጠሮ ተይዞለታል።

ሚካኤል ወደ ትምህርት ቤት ለመድረስ እና ለመመለስ እንዲሁም በክፍሉ እና በመጫወቻ ስፍራው ውስጥ በሰላም ለመዘዋወር የሚጠቀምበት ነጭ ዱላ ተሰጠው።

የድጋፍ ሰጪው ሰራተኛ ነጭ ዱላን ስለመጠቀም እና ሚካኤል በክፍል እና በመጫወቻ ስፍራው ውስጥ በደህና እንዲንቀሳቀስ እንዴት እንደሚረዱት በክፍሉ ውስጥ ያሉትን ልጆች አነጋግሮል። አሁን ሁሉም ሰው በትምህርት ቤቱ ኮሪደሮች እና መንገዶች ላይ መሰናክሎችን ላለመተው ሁልጊዜ ይሞክራሉ!

ጥያቄ

  • ሚካኤል ነጭ ዱላውን እንዲያገኝ እና እንዲጠቀም የረዱት ሰዎች እነማን ነበሩ?
  • እያንዳንዱ ሰው ምን ሚና ተጫውቷል?
  • ድርጅቱን ያነጋገሩ እና በጉብኝቱ ወቅት ሚካኤልን የሚደግፉ የሚካኤል ወላጆች
  • ሚካኤልን የጎበኘው የማህበረሰቡ ድጋፍ ሰጭ እና ግምገማ እንዲደረግለት አመቻችቶል
  • ሚካኤል በራሱ መንቀሳቀስ እንደሚፈልግ ገልጿል።
  • የሚካኤል አስተማሪዎች እና የክፍል ጓደኞቹ በትምህርት ቤት ነጩን ዱላ ሲጠቀም እየደገፉት እና በኮሪደሮች እና በመንገዶቹ ላይ ያሉ እንቅፋቶችን ለመቀነስ እየሰሩ ነው።

ማቲያስ እና ሚስቱ በጤና ክሊኒክ ተቀምጠው ነርስ ሲያወሩ።

ማቲያስን አስታውስ?
ማቲያስ የስኳር በሽታ አለበት እና በአካባቢው የጤና ክሊኒክ ውስጥ ከነርስ ጋር መደበኛ ቀጠሮዎች አሉት።

በአንድ ቀጠሮ ወቅት ነርሷ ማቲያስ በእግር ሲራመድ የተረጋጋ እንዳልሆነ አስተውላለች። ማቲያስ ቶሎ ስለሚደክመው መራመድ እንደሚከብደው ገለጸ።

ነርሷ ማቲያስን ወደ ክሊኒኩ የማህበረሰብ ሰራተኛ ሪፈር አድርጋለች። የማህበረሰቡ ሰራተኛው የእንቅስቃሴ ማጣሪያ ምርመራ ካደረገ በኃላ ማቲያስ የመራመጃ አጋዥ ቢጠቀም ተጠቃሚ እንደሚሆን ተገንዝቦል እና እግሩ እንዳይጎዳ ለመከላከል የሚለብሱ ተስማሚ ጫማዎች ላይ መክሮታል። ከመራመጃ አጋዥ ግምገማ በኋላ የማህበረሰብ ሰራተኛው ለማቲያስ ሮሌተር ሰጠው።

ማቲያስ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የመራመጃ አጋዥ መሣሪያን የተጠቀመ ሁለተኛው ሰው ነበር። የቤተክርስቲያኑ ኮሚቴ ለሁሉም ሰው ተደራሽ ለማድረግ የተጋደመ መወጣጫ ለመስራት ወሰኖል።

በክሊኒኩ ውስጥ በተደረገ የክትትል ቀጠሮ ወቅት፤ የማህበረሰቡ ሰራተኛ ማቲያስ የራሱን እንክብካቤ እንዴት እንደሚያስተዳድር (እንደ መጸዳጃ ቤት መሄድ እና/ወይም እራሱን ማጠብ) ጠይቆት ነበር። ማቲያስ የሽንት መቆጣጠር ችግር ስላጋጠመው ወደ ውጭ መውጣት እንዳቆመ ተናግሯል። በነርሷ ከተገመገመ በኋላ፤ ማቲያስ ወደ ማህበረሰቡ በሚወጣበት ጊዜ የሚጠቅሙ የሚስቡ ጨርቆችን(absorbent cloths) ቀርቦለታል። አሁን ማቲያስ ወደ ውጭ ለመውጣት በራስ የመተማመን አለው።

ጥያቄ

  • ማቲያስ ረዳት ምርቶችን እንዲያገኝ እና እንዲጠቀም በመርዳት ላይ የተሳተፉት እነማን ነበሩ?
  • እያንዳንዱ ሰው ምን ሚና ተጫውቷል?
  • ማቲያስ ከረዳት ምርቶች እንደሚጠቀም ያስተዋለችው ነርስ። ለእንቅስቃሴ ማጣሪያ ምርመራ ወደ አንድ የማህበረሰብ ሰራተኛ ሪፈር አድርጋዋለች እና በኋላም ሽንት ያለመቆጣጠር ችግሩን በመገምገም ረድታለች።
  • መራመጃ አጋዥ ለማቅረብ የገመገመው የማህበረሰብ ሰራተኛ፤ ስለራስ እንክብካቤ ፍላጎቱ ማቲያስን ጠየቀው።
  • ማቲያስ መራመድ እየከበደው እንደሆነ እና ሽንቱን መቆጣጠር ባለመቻሉ ምክንያት ወደ ውጭ መውጣት እንደማይፈልግ አስረድቷል።
  • በቤተክርስቲያን ውስጥ የመራመጃ አጋዡን በተሳካ ሁኔታ መጠቀም እንደሚችል ያረጋገጠለት የቤተክርስቲያኑ ማህበረሰብ።

ከዚህ ቀደም እንዳየነው ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን የረዳት ምርቶች እንዲያገኙ በመደገፍ ሚና የሚጫወቱ ብዙ ሰዎች አሉ።

ትምህርት ሁለትን ጨርሰሃል!

0%
በረዳት ምርት አቅርቦት ውስጥ የተለያዩ ሚናዎች
ትምህርት፡- 2 የ 5
ርዕስ፡- 1 የ 1